የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb18 ግንቦት ገጽ 8
  • “አምላክ ያጣመረውን . . .”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “አምላክ ያጣመረውን . . .”
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ላቋቋመው የጋብቻ ዝግጅት አክብሮት ይኑራችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • መፍትሄው መፋታት ነው?
    ንቁ!—2004
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
mwb18 ግንቦት ገጽ 8
አንድ ወንድና ሴት እጅ ለእጅ ተያይዘው

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“አምላክ ያጣመረውን . . .”

አንድ ሰው ሚስቱን ሊፈታ ካሰበ ሕጋዊ የምሥክር ወረቀት ማዘጋጀት እንዳለበት የሙሴ ሕግ ያዛል። ይህም ሰዎች ቸኩለው ጋብቻቸውን እንዳያፈርሱ ይከላከላል። ሆኖም በኢየሱስ ዘመን የነበሩ የሃይማኖት መሪዎች ፍቺ መፈጸም ቀላል እንዲሆን አድርገው ነበር። አንድ ሰው ሚስቱን በፈለገው ምክንያት መፍታት ይችል ነበር። (nwtsty ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች—ማር 10:4, 11) ኢየሱስ የጋብቻ ዝግጅት እንዲቋቋም ያደረገው ይሖዋ እንደሆነ ተናግሯል። (ማር 10:2-12) ባልና ሚስት ለዘለቄታው “አንድ ሥጋ” መሆን አለባቸው። ማቴዎስ በጻፈው ተመሳሳይ ዘገባ ላይ እንደተገለጸው ለፍቺ የሚያበቃው ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያት ‘የፆታ ብልግና’ ብቻ ነው።—ማቴ 19:9

በዛሬው ጊዜ ያሉ አብዛኞቹ ሰዎች ስለ ትዳር የኢየሱስ ዓይነት ሳይሆን የፈሪሳውያን ዓይነት አመለካከት አላቸው። በዓለም ያሉ ሰዎች ችግሮች ሲነሱ ቶሎ የሚያስቡት መፋታትን ነው። ክርስቲያን ባለ ትዳሮች ግን የገቡትን የጋብቻ ቃለ መሃላ ከፍ አድርገው ይመለከቱታል፤ እንዲሁም የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተጠቅመው ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። ፍቅርና አክብሮት ቤተሰብን አንድ ያደርጋል የተባለውን ቪዲዮ ተመልከቱ፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦

  • መጽሐፍ ቅዱስ ሲነበብ፤ አንድ ባል ሚስቱ ሐሳቧን ስትገልጽ ሲያዳምጣት፤ የተቀደደ የሠርግ ፎቶ

    በትዳራችሁ ውስጥ ምሳሌ 15:1⁠ን ተግባራዊ ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? ይህን ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • ምሳሌ 19:11⁠ን ተግባራዊ ማድረግ ችግሮችን ለማስወገድ የሚረዳው እንዴት ነው?

  • ትዳራችሁ ቋፍ ላይ በሚሆንበት ጊዜ ‘ብንፋታ ይሻል ይሆን?’ ብሎ ከማሰብ ይልቅ በየትኞቹ ጥያቄዎች ላይ ማሰላሰል ይኖርባችኋል?

  • ማቴዎስ 7:12⁠ን ተግባራዊ ማድረግ ከአሁኑ የተሻለ ባል ወይም ሚስት መሆን እንድትችሉ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ