ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ ደፋር እንድትሆን ይረዳሃል
ትምህርት ቤት ውስጥ የይሖዋ ምሥክር መሆንህን መናገር ወይም ምሥራቹን መስበክ ያስፈራሃል? ከሆነ ‘እንደ ምንም ብለህ በድፍረት’ መናገር የምትችለው እንዴት ነው? (1ተሰ 2:2) እንዲህ ለማድረግ የሚያነሳሳህ ምንድን ነው? ይሖዋ ደፋር እንድትሆን ይረዳሃል የሚለውን ቪዲዮ ከተመለከትክ በኋላ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ሞክር፦
ሶፊያ ደፋር እንድትሆን የረዳት ምንድን ነው?
ሶፊያ ከቤተሰቧ ጋር ያደረገችው ልምምድ የጠቀማት እንዴት ነው?
አብረውህ ለሚማሩ ልጆች መመሥከር ያለብህ ለምንድን ነው?
በአሁኑ ወቅት በትምህርት ላይ ባትሆንም እንኳ ከዚህ ቪዲዮ ምን ትምህርት ታገኛለህ?