ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | የሐዋርያት ሥራ 27-28
ጳውሎስ በመርከብ ወደ ሮም ተጓዘ
ጳውሎስ እስረኛ ቢሆንም ስለ እምነቱ ለሌሎች ከመመሥከር ወደኋላ አላለም። በመርከብ እየተጓዙ ሳለ ለመርከበኞቹና አብረውት ለሚጓዙት መንገደኞች ምሥራቹን ሰብኳል። የመርከብ አደጋ አጋጥሟቸው ወደ ማልታ ደሴት ከደረሱ በኋላም ቢሆን ከሕመማቸው ለፈወሳቸው ሰዎች ሰብኮላቸው እንደሚሆን አያጠራጥርም። ሮም ከደረሰ ከሦስት ቀን በኋላ የአይሁዳውያንን ታላላቅ ሰዎች ጠርቶ መሥክሮላቸዋል። ጳውሎስ የቁም እስረኛ ሆኖ ለሁለት ዓመት በቆየበት ጊዜም ወደ እሱ ለመጡት ሁሉ መሥክሯል።
የተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩብህም ምሥራቹን ለመስበክ ምን ማድረግ ትችላለህ?