የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb19 የካቲት ገጽ 8
  • ጸንታችሁ በጉጉት ተጠባበቁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጸንታችሁ በጉጉት ተጠባበቁ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጽናት
    ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል
  • ማንኛውም ነገር ሽልማቱን እንዲያሳጣችሁ አትፍቀዱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • “ጽናት ሥራውን ሙሉ በሙሉ ይፈጽም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ጽናት ለክርስቲያኖች እጅግ አስፈላጊ ነው
    መጠበቂያ ግንብ—1993
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
mwb19 የካቲት ገጽ 8

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ጸንታችሁ በጉጉት ተጠባበቁ

የአምላክን መንግሥት መምጣት ለምን ያህል ጊዜ ስትጠባበቅ ቆይተሃል? የተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙህም በጽናት እየተጠባበቅክ ነው? (ሮም 8:25) አንዳንድ ክርስቲያኖች ካጋጠሟቸው ፈተናዎች መካከል ጥላቻ፣ መድልዎ፣ እስራት አልፎ ተርፎም የግድያ ዛቻ ይገኙበታል። ሌሎች ብዙዎች ደግሞ ሥር የሰደደ ሕመም ወይም የዕድሜ መግፋት የሚያስከትሉትን መከራ መቋቋም አስፈልጓቸዋል።

እኛስ መከራ እየደረሰብንም እንኳ በጉጉት ለመጠባበቅ ምን ይረዳናል? በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብና ባነበብነው ላይ በማሰላሰል እምነታችንን ማጠናከር ያስፈልገናል። በተጨማሪም በተስፋችን ላይ ትኩረት ማድረግ ይኖርብናል። (2ቆሮ 4:16-18፤ ዕብ 12:2) ወደ ይሖዋ ምልጃ ማቅረብ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ኃይል እንዲሰጠን አባታችንን መለመን አለብን። (ሉቃስ 11:10, 13፤ ዕብ 5:7) አፍቃሪው አባታችን “በትዕግሥትና በደስታ ሁሉንም ነገር በጽናት [እንድንቋቋም]” ይረዳናል።—ቆላ 1:11

‘በጽናት ሩጡ’—ሽልማቱን እንደምታገኙ እርግጠኞች ሁኑ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ጄሚ እና ባለቤቱ አገልግሎት ላይ

    በሕይወታችን ውስጥ የትኞቹ “ያልተጠበቁ ክስተቶች” ሊያጋጥሙን ይችላሉ? (መክ 9:11)

  • ጄሚ አደጋ ካጋጠመው በኋላ ወንድም ካርል ጥቅስ ሲያነብለት

    መከራዎች ሲያጋጥሙን ጸሎት የሚረዳን እንዴት ነው?

  • ጄሚ እና ካርል ለአንድ ባልና ሚስት እረኝነት ሲያደርጉ

    ይሖዋን ከዚህ ቀደም እናገለግለው የነበረውን ያህል ማገልገል ባንችል እንኳ አሁን ማድረግ በምንችለው ነገር ላይ ማተኮር ያለብን ለምንድን ነው?

  • ጄሚ በገነት ውስጥ እንደገና እንደ ልቡ መንቀሳቀስ የሚችልበትን ጊዜ በዓይነ ሕሊናው ሲመለከት

    ዓይንህ ሽልማቱ ላይ ያተኩር

    ሽልማቱን እንደምታገኝ እርግጠኛ እንድትሆን የሚረዳህ ምንድን ነው?

መከራ የደረሰባቸውን ክርስቲያኖችም ሆነ የቤተሰባቸውን አባላት መደገፍ የምትችሉት እንዴት ነው?

  • በደግነት አነጋግሯቸው፤ ከሌሎች ጋር አታወዳድሯቸው

  • በጥሞና አዳምጧቸው

  • ስለ እነሱ ጸልዩ፤ አብራችኋቸውም ጸልዩ

  • ምግብ ወይም ሌሎች የቤት ውስጥ ሥራዎችን በመሥራት አግዟቸው

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ