ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ቆሮንቶስ 7-10
የእርዳታ አገልግሎታችን
የክርስቲያኖች አገልግሎት ሁለት ገጽታዎች አሉት፤ አንደኛው “የማስታረቅ አገልግሎት” ወይም የስብከቱና የማስተማሩ ሥራችን ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ለእምነት ባልንጀሮቻችን የምንሰጠው ‘የእርዳታ አገልግሎት’ ነው። (2ቆሮ 5:18-20፤ 8:4) በመሆኑም ለአምላክ የምናቀርበው ቅዱስ አገልግሎት የተቸገሩ ክርስቲያኖችን መርዳትንም ይጨምራል። ይህን ማድረጋችን ምን ጥቅሞች አሉት?