ክርስቲያናዊ ሕይወት
የይሖዋ አመለካከት ምንድን ነው?
ትልቅም ይሁን ትንሽ ውሳኔ ከማድረጋችን በፊት ‘የይሖዋ አመለካከት ምንድን ነው?’ ብለን ራሳችንን እንጠይቃለን? መቼም ቢሆን የይሖዋን ሐሳብ ሙሉ በሙሉ ማወቅ እንደማንችል ግልጽ ነው፤ ያም ቢሆን ይሖዋ “ለማንኛውም መልካም ሥራ” ብቁ እንድንሆን የሚያስፈልገንን ነገር በቃሉ አማካኝነት ገልጾልናል። (2ጢሞ 3:16, 17፤ ሮም 11:33, 34) ኢየሱስ የይሖዋን ፈቃድ በሚገባ ያስተዋለ ከመሆኑም ሌላ በሕይወቱ ውስጥ ቅድሚያ ሰጥቶታል። (ዮሐ 4:34) እኛም የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል ይሖዋን የሚያስደስቱ ውሳኔዎች ለማድረግ የቻልነውን ያህል እንጣር።—ዮሐ 8:28, 29፤ ኤፌ 5:15-17
የይሖዋ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ (ዘሌ 19:18) የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ የሚኖርብን ለምንድን ነው?
ከሙዚቃ ምርጫ ጋር በተያያዘ የትኞቹን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ከግምት ማስገባት ይኖርብናል?
ከአለባበስና ከአጋጌጥ ጋር በተያያዘ የትኞቹን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ከግምት ማስገባት ይኖርብናል?
የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ግምት ውስጥ ማስገባት የሚጠይቁ ምን ሌሎች ሁኔታዎች አሉ?
የይሖዋ ፈቃድ ምን እንደሆነ የማስተዋል ችሎታችንን ማሻሻል የምንችለው እንዴት ነው?
የማደርጋቸው ውሳኔዎች ከይሖዋ ጋር ስላለኝ ዝምድና ምን ይጠቁማሉ?