የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb19 ሰኔ ገጽ 7
  • መዝናኛችሁን በጥበብ ምረጡ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መዝናኛችሁን በጥበብ ምረጡ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመዝናኛ ምርጫህ ይሖዋን የሚያስደስት ይሁን
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ጥሩ መዝናኛ መምረጥ የምንችለው እንዴት ነው?
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • ጤናማ መዝናኛ መምረጥ የሚቻለው እንዴት ነው?
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • ማህበራዊ መዝናኛ ጥቅሞቹን አግኙ፣ ወጥመዶቹን ግን ሽሹ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
mwb19 ሰኔ ገጽ 7

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝናኛችሁን በጥበብ ምረጡ

መዝናኛችንን በጥበብ መምረጥ ያለብን ለምንድን ነው? በአንድ ፊልም፣ ሙዚቃ፣ ድረ ገጽ፣ መጽሐፍ ወይም የቪዲዮ ጨዋታ ለመዝናናት ስንመርጥ ወደ አእምሯችን የምናስገባውን ነገር እየመረጥን ነው። ምርጫችን በባሕርያችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። የሚያሳዝነው በዛሬው ጊዜ ያለው አብዛኛው መዝናኛ ይሖዋ የሚያወግዛቸውን ነገሮች የያዘ ነው። (መዝ 11:5፤ ገላ 5:19-21) በዚህም ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ፣ ይሖዋን የሚያስከብሩ ነገሮችን ሁልጊዜ እንድናስብ ያበረታታናል።—ፊልጵ 4:8

ምን ዓይነት መዝናኛ መምረጥ ይኖርብኛል? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የሮማውያን የግላዲያተሮች ፍልሚያ

    በጥንቷ ሮም ይካሄዱ የነበሩ የግላዲያተሮች ፍልሚያዎች በዘመናችን ካሉ አንዳንድ መዝናኛዎች ጋር የሚመሳሰሉት እንዴት ነው?

  • አንድ አቅኚ ወንድም በጉባኤው ከሚገኝ ወጣት ወንድም ጋር ሲያገለግል

    ታዳጊዎችና ወጣቶች መዝናኛቸውን በጥበብ እንዲመርጡ የጉባኤው አባላት ሊረዷቸው የሚችሉት እንዴት ነው?

  • ወታደር

    ሮም 12:9⁠ን ከመዝናኛ ምርጫ ጋር በተያያዘ ግምት ውስጥ ማስገባት የምንችለው እንዴት ነው?

  • ወጣት የይሖዋ ምሥክሮች እግር ኳስ ሲጫወቱ

    በአካባቢያችሁ ምን ዓይነት ጤናማ መዝናኛዎች አሉ?

የሚያሳትፉ ወይስ ተመልካች ብቻ የሚያደርጉ መዝናኛዎች?

በዛሬው ጊዜ ያሉት አብዛኞቹ ተወዳጅ መዝናኛዎች ተመልካች መሆንን እንጂ መንቀሳቀስን የሚያበረታቱ አይደሉም። ፊልሞች፣ መጻሕፍትና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በሌላ ሰው የፈጠራ ሥራ እንድንዝናና እንጂ እኛ ተሳታፊ እንድንሆን አያደርጉም። እንዲህ ያሉት መዝናኛዎች በተወሰነ መጠን ጠቃሚ ቢሆኑም ብዙዎች፣ አሳታፊ የሆኑ መዝናኛዎች የበለጠ አስደሳች እንደሆኑ መገንዘብ ችለዋል። ለምሳሌ ያህል አንዳንዶች፣ የሙዚቃ መሣሪያ መጫወት ወይም ሥዕል መሣል ያስደስታቸዋል። ሌሎች ደግሞ ከቤት ውጪ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ በስፖርታዊ ጨዋታዎች መካፈል፣ ተራራ መውጣት ወይም የመሳሰሉት ነገሮች ያዝናኗቸዋል። የምንመርጠው መዝናኛ ምንም ይሁን ምን “ሁሉንም ነገር ለአምላክ ክብር [እናድርግ]።”—1ቆሮ 10:31

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ