ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ቆላስይስ 1-4
አሮጌውን ስብዕና ገፋችሁ ጣሉ እንዲሁም አዲሱን ስብዕና ልበሱ
ወደ እውነት ስትመጣ በሕይወትህ ውስጥ ብዙ ለውጦች አድርገሃል? እንዲህ በማድረግህ ይሖዋ እንደተደሰተ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። (ሕዝ 33:11) ሆኖም አሮጌው ስብዕና እንዳያገረሽብህ ለመከላከል እንዲሁም አዲሱን ስብዕና እንደለበስክ ለመኖር ያልተቋረጠ ጥረት ማድረግ ያስፈልግሃል። ማስተካከያ ማድረግ የሚያስፈልግህ በየትኞቹ አቅጣጫዎች እንደሆነ ለማወቅ እስቲ ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦
ቂም የያዝኩበት ሰው አለ?
በጣም በቸኮልኩበት ወይም በደከመኝ ጊዜም እንኳ ትዕግሥት አሳያለሁ?
የብልግና ሐሳብ ቢመጣብኝ ወዲያውኑ ከአእምሮዬ ለማውጣት እሞክራለሁ?
ከእኔ የተለየ ዘር ወይም ዜግነት ላላቸው ሰዎች አሉታዊ አመለካከት አለኝ?
በቅርብ ጊዜ ውስጥ በቁጣ ገንፍዬ ወይም ደግነት የጎደለው ነገር ተናግሬ አውቃለሁ?