ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 1 ተሰሎንቄ 1-5
“እርስ በርስ ተበረታቱ እንዲሁም እርስ በርስ ተናነጹ”
እያንዳንዱ ክርስቲያን ሌሎችን ማበረታታት ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ አዘውትረን በስብሰባዎች ላይ መገኘታችንና በአገልግሎት መካፈላችን የእምነት ባልንጀሮቻችንን ያበረታታቸዋል፤ ምናልባትም ይህን የምናደርገው በጤና እክል ወይም በሌሎች ችግሮች የተነሳ “ከፍተኛ ተጋድሎ” እያደረግን ይሆናል። (1ተሰ 2:2 ግርጌ) ከዚህም በተጨማሪ ማበረታቻ የሚያስፈልጋቸው ወንድሞቻችንን ለማበረታታት ምን ማለት እንደምንችል አስቀድመን በማሰብና ከተቻለ ደግሞ ምርምር በማድረግ፣ እነሱን የሚያጽናና ሐሳብ መናገር እንችላለን።
አስቸጋሪ ሁኔታ የገጠመውን አንድ ክርስቲያን ለማበረታታት የሚረዱ ጠቃሚ ሐሳቦችን የት ማግኘት ትችላለህ?
ከጉባኤህ አባላት መካከል ማንን ማበረታታት ትፈልጋለህ?