ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለአምላክ ማደር ወይስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ?
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጠቃሚ ነው? አዎ፣ ጥቅሙ ግን መንፈሳዊ ሥልጠና ከሚያስገኘው ጥቅም ጋር የሚወዳደር አይደለም። (1ጢሞ 4:8) በመሆኑም ክርስቲያኖች ስፖርትን በተመለከተ ሚዛናዊ መሆን አለባቸው።
ስፖርታዊ ጨዋታዎችን በተመለከተ ምን ማወቅ ይኖርብሃል? የሚለውን የነጭ ሰሌዳ አኒሜሽን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
1. ስፖርት የትኞቹን ክህሎቶች እንድታዳብር ይረዳሃል?
2. ከስፖርት ጥቅም ማግኘታችን የተመካው በየትኞቹ ሦስት ነገሮች ላይ ነው?
3. በየትኞቹ ስፖርታዊ ጨዋታዎች መካፈል እና የትኞቹን ስፖርቶች መመልከት እንዳለብን ለመወሰን መዝሙር 11:5 የሚረዳን እንዴት ነው?
4. በስፖርታዊ ጨዋታዎች ከምንካፈልበት መንገድ ጋር በተያያዘ በፊልጵስዩስ 2:3 እና በምሳሌ 16:18 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
5. ፊልጵስዩስ 1:10 በስፖርታዊ ጨዋታዎች በመካፈል ወይም ጨዋታዎቹን በመመልከት ጊዜ እንዳናባክን የሚረዳን እንዴት ነው?