ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ቲቶ 1–ፊልሞና
‘ሽማግሌዎችን ሹም’
ቲቶ “በየከተማው ሽማግሌዎችን [እንዲሾም]” ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር። በዛሬው ጊዜ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች በጉባኤ ውስጥ ወንዶችን የሚሾሙት ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሠራር መሠረት በማድረግ ነው።
የበላይ አካል
የበላይ አካሉ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረውን አሠራር በመከተል፣ ሽማግሌዎችንና የጉባኤ አገልጋዮችን የመሾሙን ከባድ ኃላፊነት ለወረዳ የበላይ ተመልካቾች በአደራ ሰጥቷል።
የወረዳ የበላይ ተመልካቾች
እያንዳንዱ የወረዳ የበላይ ተመልካች በሽማግሌዎች የቀረበለትን የድጋፍ ሐሳብ በጥንቃቄና በጸሎት ከመረመረ በኋላ ብቃቱን የሚያሟሉትን ወንድሞች ይሾማል።
የተሾሙት ሽማግሌዎች
ሽማግሌዎች ከተሾሙ በኋላም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት ብቃቶች ጋር ተስማምተው ለመኖር ጥረት ማድረጋቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋል።