ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ ንጹሕ ሰዎችን ይወዳል
ብዙ ወላጆች “እጅህን ታጠብ፤ ክፍልህን አጽዳ፤ መሬቱን ጥረግ፤ ቆሻሻውን ድፋ” እንደሚሉት ያሉ መመሪያዎችን በመስጠት ልጆቻቸው ንጽሕናቸውን እንዲጠብቁ ያስተምራሉ። ይሁንና እነዚህ የንጽሕና መሥፈርቶች የመነጩት ቅዱስ ከሆነው አምላካችን ነው። (ዘፀ 30:18-20፤ ዘዳ 23:14፤ 2ቆሮ 7:1) ሰውነታችንንም ሆነ ንብረታችንን በንጽሕና ስንይዝ ይሖዋን እናስከብራለን። (1ጴጥ 1:14-16) ቤታችንንና አካባቢያችንን በተመለከተስ ምን ማለት ይቻላል? በየመንገዱና በየመናፈሻው ቆሻሻ ከሚጥሉ ሰዎች በተለየ እኛ ክርስቲያኖች መኖሪያችን የሆነችውን ምድርን ላለማቆሸሽ እንጠነቀቃለን። (መዝ 115:16፤ ራእይ 11:18) የከረሜላ ልጣጭ፣ የውኃ መያዣ ፕላስቲክ ወይም ማስቲካ እንደምንጥልበት መንገድ ያሉ ትናንሽ ነገሮች እንኳ ለንጽሕና ያለንን አመለካከት ያሳያሉ። በሁሉም የሕይወታችን ዘርፎች “ራሳችንን ብቁ የአምላክ አገልጋዮች አድርገን” ማቅረብ እንፈልጋለን።—2ቆሮ 6:3, 4
አምላክ ንጹሕ ሰዎችን ይወዳል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
አንዳንዶች ንብረታቸውን በንጽሕና ላለመያዝ ምን ሰበብ ሊያቀርቡ ይችላሉ?
የሙሴ ሕግ ይሖዋ ለንጽሕና ያለውን አመለካከት የሚያሳየው እንዴት ነው?
ምንም ነገር መናገር ሳያስፈልገን ስለ ይሖዋ መመሥከር የምንችለው እንዴት ነው?
ይሖዋ ለንጽሕና ያለውን አመለካከት በግል ሕይወቴ ማንጸባረቅ የምችለው እንዴት ነው?