ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ዮሐንስ 1-13፤ 3 ዮሐንስ 1-14–ይሁዳ 1-25
እውነት ውስጥ ለመቆየት ብርቱ ተጋድሎ ማድረግ አለብን
ኢየሱስ “በጠባቡ በር ለመግባት ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጉ” የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቷል። (ሉቃስ 13:24) ኢየሱስ የተናገረው ሐሳብ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ብርቱ ትግል ማድረግ እንደሚያስፈልገን ይጠቁማል። የኢየሱስ ወንድም ይሁዳም ‘ለእምነት ብርቱ ተጋድሎ አድርጉ’ በማለት በመንፈስ መሪነት ጽፏል። የሚከተሉትን ነገሮች ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ያስፈልጋል፦
ከፆታ ብልግና ለመራቅ።—ይሁዳ 6, 7
በኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉትን ለማክበር።—ይሁዳ 8, 9
“እጅግ ቅዱስ” በሆኑት ክርስቲያናዊ ትምህርቶች ላይ ያለንን እምነት ለማጠናከር።—ይሁዳ 20, 21