ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ራእይ 20-22 “እነሆ፣ ሁሉንም ነገር አዲስ አደርጋለሁ” 21:1-5 ይሖዋ ሁሉንም ነገር አዲስ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል። “አዲስ ሰማይ”፦ በምድር ላይ ጽድቅ እንዲሰፍን የሚያደርግ አዲስ መስተዳድር “አዲስ ምድር”፦ የአምላክን አገዛዝ የሚቀበልና በእሱ የጽድቅ መሥፈርቶች የሚመራ ማኅበረሰብ ‘ሁሉም ነገር አዲስ ይሆናል’፦ ሁሉም ዓይነት አካላዊ፣ አእምሯዊና ስሜታዊ ሥቃይ በየቀኑ በምናሳልፈው አስደሳች ሕይወት ይተካል