ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 15-17
ይሖዋ የአብራምንና የሦራን ስም የቀየረው ለምንድን ነው?
ይሖዋ አብራምን እንከን የለሽ እንደሆነ አድርጎ ተመልክቶታል። ለአብራም የገባለትን ቃል ኪዳን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በሰጠበት ጊዜ ለአብራምና ለሦራ ትንቢታዊ ትርጉም ያዘለ ስም አውጥቶላቸዋል።
ከስማቸው ትርጉም ጋር በሚስማማ መልኩ አብርሃም የብዙ ብሔራት አባት፣ ሣራ ደግሞ የነገሥታት ቅድመ አያት ሆናለች።
አብርሃም
የብዙ ሕዝብ አባት
ሣራ
ልዕልት
ስንወለድ የሚሰጠንን ስም የምንመርጠው እኛ አይደለንም። ሆኖም ልክ እንደ አብርሃምና እንደ ሣራ መልካም ስም ማትረፋችን የተመካው በእኛ ላይ ነው። እስቲ ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦
‘በይሖዋ ፊት እንከን የለሽ መሆን የምችለው እንዴት ነው?’
‘በይሖዋ ዘንድ ምን ዓይነት ስም እያተረፍኩ ነው?’