ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 20-21
ይሖዋ ምንጊዜም የገባውን ቃል ይፈጽማል
አብርሃምና ሣራ ጠንካራ እምነት እንዳላቸው ስላሳዩ ይሖዋ ወንድ ልጅ በመስጠት ባርኳቸዋል። ከጊዜ በኋላ ፈታኝ ሁኔታ ባጋጠማቸው ወቅት ታዛዥ መሆናቸው ይሖዋ የወደፊቱን ጊዜ አስመልክቶ በገባው ቃል ላይ ጠንካራ እምነት እንዳላቸው ያሳያል።
ፈታኝ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙኝ ታዛዥ መሆኔ ይሖዋ የወደፊቱን ጊዜ አስመልክቶ በገባው ቃል ላይ እምነት እንዳለኝ የሚያሳየው እንዴት ነው? እምነቴን ማጠናከር የምችለው እንዴት ነው?