ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 27-28 ያዕቆብ የሚገባውን በረከት አገኘ 27:6-10, 18, 19, 27-29 ይስሐቅ ያዕቆብን የባረከው በረከት ትንቢታዊ ትርጉም ነበረው። 27:28—ይሖዋ ለያዕቆብ ዘሮች “ወተትና ማር የምታፈሰውን” ለም ምድር ሰጥቷቸዋል።—ዘዳ 26:15 27:29—እስራኤላውያን (የያዕቆብ ዘሮች) ከኤዶማውያን (ከኤሳው ዘሮች) የበለጠ ኃያል ሆነዋል።—ዘፍ 25:23፤ 2ሳሙ 8:14 27:29—ኤዶማውያን ለእስራኤላውያን ጥላቻ ስለነበራቸው ተረግመዋል፤ ከጊዜ በኋላ ደግሞ መላው ብሔር ጠፍቷል።—ሕዝ 25:12-14