የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb20 ሚያዝያ ገጽ 7
  • ‘ባዕዳን አማልክትን አስወግዱ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ባዕዳን አማልክትን አስወግዱ’
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምትሃታዊ ነገሮች ጉዳት አላቸው?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • በይሖዋ እርዳታ ክፉ መናፍስትን ተቃወሙ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • መጽሐፍ ቅዱስ መናፍስታዊ ድርጊቶችን በተመለከተ ምን ያስተምራል?
    ንቁ!—2017
  • ይሖዋን ብቻ አምልኩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
mwb20 ሚያዝያ ገጽ 7
አንድ ሰው ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ተያያዥነት ያለውን ጨሌ አውጥቶ ሲጥል

ክርስቲያናዊ ሕይወት

‘ባዕዳን አማልክትን አስወግዱ’

ያዕቆብ የኖረው ይሖዋ ስለ ጣዖት አምልኮ ሕግ ከመስጠቱ በፊት ቢሆንም ሊመለክ የሚገባው ይሖዋ ብቻ እንደሆነ ተገንዝቦ ነበር። (ዘፀ 20:3-5) በመሆኑም ይሖዋ በነገረው መሠረት ወደ ቤቴል ሲመለስ ያዕቆብ፣ ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ጣዖቶቻቸውን ሁሉ እንዲያስወግዱ አዟቸዋል። ከዚያም ያዕቆብ ጉትቻዎችን (እንደ ክታብ ያሉ ነገሮች ሳይሆኑ አይቀሩም) ጨምሮ ጣዖቶቻቸውን አስወገደ። (ዘፍ 35:1-4) ይሖዋ፣ ያዕቆብ በወሰደው እርምጃ እንደተደሰተ ምንም ጥርጥር የለውም።

በዛሬው ጊዜስ ይሖዋን ብቻ ማምለክ የምንችለው እንዴት ነው? ዋነኛው መንገድ፣ ከጣዖት አምልኮ ወይም ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ንክኪ ካለው ማንኛውም ነገር መራቅ ነው። ይህ ደግሞ ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ንክኪ ያላቸውን ዕቃዎች ማስወገድንና የመዝናኛ ምርጫችንን በጥንቃቄ መመርመርን ይጠይቃል። ለምሳሌ ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘የምዝናናባቸው መጻሕፍት ወይም ፊልሞች ስለ ቫምፓየሮች፣ ዞምቢዎች ወይም እነዚህን ስለመሳሰሉ ነገሮች የሚያወሱ ናቸው? አስማትን፣ ድግምትን ወይም ሟርትን ምንም ጉዳት እንደሌለው መዝናኛ አድርገው ያቀርባሉ?’ ይሖዋ ከሚጠላው ከማንኛውም ነገር መራቅ አለብን።—መዝ 97:10

‘ዲያብሎስን ተቃወሙት’ የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • እጁ ላይ ክታብ የታሰረለት ልጅ አልጋ ላይ ተኝቶ። ከበስተጀርባ መጽሐፍ ቅዱስን እያጠናች ያለችው የልጁ እናት መጽሐፍ ቅዱስን ከሚያስጠኗት ባልና ሚስት ጋር እየተነጋገረች ነው

    ፓሌሳ የተባለች የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ በሕይወቷ ውስጥ ምን ችግር አጋጥሟት ነበር?

  • ባልና ሚስቱ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታቸው እርዳታ ለማግኘት ሁለት ሽማግሌዎችን ሲያማክሩ

    ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር የተያያዘ ችግር ሲያጋጥመን የሽማግሌዎችን እርዳታ መጠየቃችን የጥበብ እርምጃ የሆነው ለምንድን ነው?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቷ የልጁን ክታብ ምድጃ ውስጥ ከትታ ስታቃጥለው

    ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ እንዲሁም ወደ አምላክ ቅረቡ—ያዕ 4:7, 8

    የይሖዋን ጥበቃ ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ከየትኞቹ ነገሮች ሙሉ በሙሉ መራቅ አለባቸው?

  • ፓሌሳ ምን ቆራጥ እርምጃ ወስዳለች?

  • እናንተ በምትኖሩበት አካባቢ ከአጋንንት ተጽዕኖ መራቅ የሚቻልባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ