ክርስቲያናዊ ሕይወት
ዝግጁ ናችሁ?
በአካባቢያችሁ የተፈጥሮ አደጋ ቢከሰት ዝግጁ ናችሁ? እንደ መሬት መንቀጥቀጥ፣ አውሎ ነፋስ፣ ሰደድ እሳት እና ጎርፍ ያሉ አደጋዎች በድንገት ሊከሰቱ የሚችሉ ሲሆን ብዙ ጥፋት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ከዚህም በተጨማሪ የአሸባሪዎች ጥቃት፣ ረብሻና ወረርሽኝ በማንኛውም ስፍራ ሳይታሰብ ሊያጋጥም ይችላል። (መክ 9:11) እንዲህ ያሉ ነገሮች እኛ ባለንበት አካባቢ ፈጽሞ ሊያጋጥሙ አይችሉም ብለን ማሰብ አይኖርብንም።
እያንዳንዳችን ለአደጋ አስቀድመን ለመዘጋጀት ተግባራዊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ አለብን። (ምሳሌ 22:3) እርግጥ ነው፣ የይሖዋ ድርጅት አደጋ በሚያጋጥምበት ጊዜ የተወሰነ ድጋፍ ለመስጠት ጥረት ያደርጋል፤ ይህ ሲባል ግን ከእኛ የሚጠበቅ ምንም ነገር የለም ማለት አይደለም።—ገላ 6:5
የተፈጥሮ አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ለአደጋ ጊዜ ራሳችንን በመንፈሳዊ ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?
የሚከተሉትን ነገሮች ማድረጋችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
• አደጋ ከመከሰቱ በፊት፣ በአደጋው ወቅትም ሆነ ከአደጋው በኋላ ከሽማግሌዎች ጋር ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ
• ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ሻንጣ ማዘጋጀት—g17.5 6
• ምን ዓይነት አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉና በእያንዳንዱ ሁኔታ ሥር ምን ማድረግ እንዳለብን መወያየት
አደጋ ያጋጠማቸውን መርዳት የምንችልባቸው ሦስት መንገዶች የትኞቹ ናቸው?