ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 6–7
“አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ”
ይሖዋ በግብፅ ላይ መቅሰፍት ከማምጣቱና እስራኤላውያንን ከባርነት ነፃ ከማውጣቱ በፊት፣ ለማድረግ ያሰበውን ነገር ለእስራኤላውያን ነግሯቸዋል። እስራኤላውያን ከዚያ በፊት አይተው በማያውቁት መንገድ የይሖዋን ኃይል ያያሉ፤ ግብፃውያንም የይሖዋን ማንነት ለማወቅ ይገደዳሉ። ይሖዋ የገባው ቃል ሲፈጸም የእስራኤላውያን እምነት ተጠናክሯል፤ ይህም በግብፅ ሳሉ አጋጥሟቸው የነበረውን የሐሰት ሃይማኖት ተጽዕኖ ከአእምሯቸው ለማውጣት ረድቷቸዋል።
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ አምላክ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሰጣቸው ተስፋዎች እንደሚፈጸሙ ያለህን እምነትህን የሚያጠናክረው እንዴት ነው?