ክርስቲያናዊ ሕይወት
ትሑት ሁኑ—ጉራ አትንዙ
ጉራ መንዛት ወይም ራስን ማወደስ ኩራተኛ እንደሆንን የሚያሳይ ከመሆኑም ሌላ የሚሰማውንም ሰው አያንጽም። መጽሐፍ ቅዱስ “የገዛ አፍህ ሳይሆን ሌላ ሰው ያመስግንህ” የሚል ምክር የሚሰጠው ለዚህ ነው።—ምሳሌ 27:2
የይሖዋ ወዳጅ ሁን—ትሑት ሁን የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ሰዎች ብዙ ጊዜ ስለ የትኞቹ ነገሮች ጉራ ይነዛሉ?
ካሌብ ለጓደኛው በጉራ የተናገረው ስለ ምንድን ነው?
የካሌብ አባት ካሌብን ያስረዳው እንዴት ነው?
አንደኛ ጴጥሮስ 5:5 ትሑት እንድንሆን የሚረዳን እንዴት ነው?