ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 19–20
አሥርቱ ትእዛዛት ለአንተ ምን ትርጉም አላቸው?
ክርስቲያኖች በሙሴ ሕግ ሥር አይደሉም። (ቆላ 2:13, 14) ታዲያ አሥርቱ ትእዛዛትም ሆኑ ሌሎቹ ሕጎች በዛሬው ጊዜ ምን ጥቅም አላቸው?
በአንዳንድ ጉዳዮች ረገድ የይሖዋን አመለካከት ያሳውቁናል
ይሖዋ ከእኛ ምን እንደሚጠብቅብን ያስገነዝቡናል
ሌሎችን እንዴት መያዝ እንዳለብን ያስተምሩናል
ከአሥርቱ ትእዛዛት ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?