የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb20 ጥቅምት ገጽ 5
  • ወጣቶች—ይሖዋ የቅርብ ጓደኛችሁ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወጣቶች—ይሖዋ የቅርብ ጓደኛችሁ ነው?
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የይሖዋ ወዳጅ መሆን ትችላለህ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • አምላክ ወዳጁ እንድትሆን ይጋብዝሃል
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • የጓደኛዬን ስህተት መናገር ይኖርብኛል?
    ንቁ!—2008
  • ጥሩ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ሰው ነው?
    ንቁ!—2014
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
mwb20 ጥቅምት ገጽ 5
አንድ ወጣት ዴስኩ ጋ ተቀምጦ ትኩረቱ ሳይከፋፈል የግል ጥናት እያደረገ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ወጣቶች—ይሖዋ የቅርብ ጓደኛችሁ ነው?

ምን ዓይነት ባሕርይ ያለው ጓደኛ ቢኖራችሁ ደስ ይላችኋል? ጓደኛችሁ ታማኝ፣ ደግና ለጋስ ቢሆን እንደምትደሰቱ ጥያቄ የለውም። ይሖዋ እነዚህ ባሕርያት በሙሉ አሉት። (ዘፀ 34:6፤ ሥራ 14:17) ወደ እሱ ስትጸልዩ ይሰማችኋል። የእሱን እገዛ ስትፈልጉ ሊረዳችሁ ዝግጁ ነው። (መዝ 18:19, 35) እንዲሁም ስህተት ስትሠሩ ይቅር ይላችኋል። (1ዮሐ 1:9) ይሖዋ በእርግጥም ጥሩ ጓደኛ ነው!

ከይሖዋ ጋር ጓደኝነት መመሥረት የምትችሉት እንዴት ነው? ቃሉን በማንበብ ስለ እሱ ተማሩ። የልባችሁን ግልጥልጥ አድርጋችሁ ንገሩት። (መዝ 62:8፤ 142:2) እሱ ከፍ አድርጎ ለሚመለከታቸው ነገሮች ትልቅ ቦታ እንደምትሰጡ አሳዩ፤ ከእነዚህ መካከል ልጁ፣ መንግሥቱና ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሰጣቸው ተስፋዎች ይገኙበታል። ስለ እሱ ለሌሎች ተናገሩ። (ዘዳ 32:3) ከይሖዋ ጋር የቅርብ ወዳጅነት ከመሠረታችሁ እሱ ለዘላለም ጓደኛችሁ ይሆናል።—መዝ 73:25, 26, 28

ወጣቶች—“ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘ወጣቶች—ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። አንዲት ወጣት እህት የግል ጥናቷን ከመጀመሯ በፊት ስትጸልይ።

    ራሳችሁን ወስናችሁ ለመጠመቅ መዘጋጀት የምትችሉት እንዴት ነው?

  • ‘ወጣቶች—ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። አንድ አቅኚ ካረን (ስጋው) በተባለው ቋንቋ ለአንድ ሰው ጥቅስ ሲያነብ።

    በጉባኤው ውስጥ ያሉ ወንድሞችና እህቶች ለይሖዋ በምታቀርቡት አገልግሎት ረገድ ሊረዷችሁ የሚችሉት እንዴት ነው?

  • ‘ወጣቶች—ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። በዕድሜ ትልቅ የሆኑ ወንድሞችን እገዛ ማግኘት የሚያስደስተው አንድ ወጣት ወንድም ከአንድ አረጋዊ ወንድም ጋር በመስክ አገልግሎት ሲካፈል።

    አገልግሎት ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ዝምድና የሚያጠናክረው እንዴት ነው?

  • ‘ወጣቶች—ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። አንዲት እህት ከቤቷ የሁለት ሰዓት መንገድ በእግሯ ተጉዛ መስማት የተሳናትን ሴት ስታስጠና።

    ለዘላለም የይሖዋ ጓደኛ ሆኖ መኖር ይቻላል!

    የትኞቹ የአገልግሎት መስኮች ተከፍተውላችኋል?

  • ከይሖዋ ባሕርያት መካከል የምትወዱት የትኛውን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ