የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 ጥር ገጽ 5
  • ትዳራችሁን ታደጉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትዳራችሁን ታደጉ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ክርስቲያኖች ትዳራቸውን የሰመረ ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ትዳር በቋፍ ላይ በሚሆንበት ጊዜ
    ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
  • ከሠርጋችሁ ቀን በኋላ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 ጥር ገጽ 5
አንድ ባል ከባለቤቱ ጋር መሬት ላይ ቁጭ ብሎ አብሯት ደስ እያለው ልብስ ሲያጥብ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ትዳራችሁን ታደጉ

ይሖዋ የጋብቻ ቃለ መሐላን ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል። ባለትዳሮች አንዳቸው ከሌላው ጋር መጣበቅ እንዳለባቸው ገልጿል። (ማቴ 19:5, 6) ብዙዎቹ የአምላክ አገልጋዮች አስደሳች ትዳር አላቸው። ሆኖም ፍጹም የሆነ ትዳር የለም። በትዳር ውስጥ ችግሮች ማጋጠማቸው አይቀርም። በዚህ ጊዜ፣ ባለትዳሮች ችግር ካጋጠማቸው መፍትሔው መለያየት ወይም መፋታት ነው የሚለው የተለመደ አመለካከት እንዳይጋባብን መጠንቀቅ ይኖርብናል። ታዲያ ያገቡ ክርስቲያኖች ትዳራቸውን መታደግ የሚችሉት እንዴት ነው?

አምስት ጠቃሚ እርምጃዎችን እንመልከት።

  1. ማሽኮርመምና ሥነ ምግባር የጎደለው መዝናኛ የትዳርን ጥምረት ያዳክማሉ፤ በመሆኑም እንደነዚህ ካሉት ነገሮች በመራቅ ልባችሁን ጠብቁ።—ማቴ 5:28፤ 2ጴጥ 2:14

  2. ከአምላክ ጋር ያላችሁን ወዳጅነት አጠናክሩ፤ እንዲሁም ትዳራችሁ እሱን የሚያስደስት እንዲሆን ቁርጥ ውሳኔ አድርጉ።—መዝ 97:10

  3. ምንጊዜም አዲሱን ስብዕና ለመልበስ ጥረት አድርጉ፤ እንዲሁም ትናንሽ ቢመስሉም እንኳ የትዳር ጓደኛችሁን የሚጠቅሙ የደግነት ድርጊቶችን አከናውኑ።—ቆላ 3:8-10, 12-14

  4. አክብሮት በተሞላበት መንገድ አዘውትራችሁ ትርጉም ያለው የሐሳብ ልውውጥ አድርጉ።—ቆላ 4:6

  5. ለትዳር ጓደኛችሁ የሚገባውን የምታደርጉለት በፍቅር ይሁን።—1ቆሮ 7:3, 4፤ 10:24

ክርስቲያኖች ለትዳራቸው አክብሮት በማሳየት የጋብቻ መሥራች ለሆነው ለይሖዋ አክብሮት ማሳየት ይችላሉ።

‘በጽናት ሩጡ’—የውድድሩን ሕግ አክብሩ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • “በጽናት ሩጡ’—የውድድሩን ሕግ አክብሩ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ወንድም ካሉ እና ባለቤቱ በስብሰባ አዳራሹ የጋብቻ ንግግር ከተሰጣቸው በኋላ ፈገግ ብለው።

    አንድ ትዳር ጥሩ አጀማመር ቢኖረውም እንኳ ምን ዓይነት ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ?

  • “በጽናት ሩጡ’—የውድድሩን ሕግ አክብሩ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ወንድም ካሉ እና ባለቤቱ ተረጋግተው ስለ ችግሮቻቸው ሲወያዩ። ጠረጴዛው ላይ የተገለጠ መጽሐፍ ቅዱስ አለ።

    ባልና ሚስት በመካከላቸው ያለው ፍቅር እንደጠፋ በሚሰማቸው ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የሚረዷቸው እንዴት ነው?

  • “በጽናት ሩጡ’—የውድድሩን ሕግ አክብሩ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ወንድም ካሉ ለባለቤቱና ለሁለት ልጆቹ ‘የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ’ የተባለውን መጽሐፍ ሲያነብላቸው።

    ትዳራችሁ አስደሳች እንዲሆን የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በሥራ ላይ አውሉ

    ይሖዋ ከጋብቻ ጋር በተያያዘ ምን መመሪያዎችን ሰጥቷል?

  • ትዳር የሰመረ እንዲሆን ባልም ሆነ ሚስት ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ