የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 ጥር ገጽ 11
  • ይሖዋን ለማገልገል ምረጡ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋን ለማገልገል ምረጡ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ጥምቀት—ከክርስቲያኖች የሚጠበቅ ብቃት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • ለመጠመቅ የሚያስችለውን ብቃት ማሟላት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ጥምቀትና ከአምላክ ጋር ያለህ ዝምድና
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 ጥር ገጽ 11
ይሖዋን በማገልገል የምንመራውን ሕይወት የሚያመለክት ጠመዝማዛ መንገድ። በመንገዱ ላይ ያሉት ምልክቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናትን፣ ስብሰባ መገኘትን፣ መስበክንና መጠመቅን ያመለክታሉ።

ወደ ጥምቀት በሚወስደው መንገድ ላይ የቱ ጋ ደርሰሃል?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋን ለማገልገል ምረጡ

በእውነት ቤት ውስጥ ያደግክ ወጣት አሊያም ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ነህ? ከሆነ የመጠመቅ ግብ አለህ? ለመሆኑ የመጠመቅ ግብ ማውጣት ያለብህ ለምንድን ነው? ራስን መወሰንና መጠመቅ ከይሖዋ ጋር ልዩ ዝምድና ለመመሥረት ያስችላል። (መዝ 91:1) እንዲሁም መዳን ያስገኛል። (1ጴጥ 3:21) ታዲያ እድገት አድርገህ እዚህ ግብ ላይ መድረስ የምትችለው እንዴት ነው?

እውነትን ማግኘትህን አረጋግጥ። ጥያቄ ሲፈጠርብህ ምርምር አድርግ። (ሮም 12:2) ማስተካከያ ማድረግ የሚያስፈልግህን አቅጣጫዎች ለይተህ እወቅ፤ እንዲሁም ይሖዋን ለማስደሰት ያለህ ፍላጎት አስፈላጊውን ማስተካከያ ለማድረግ ያነሳሳህ። (ምሳሌ 27:11፤ ኤፌ 4:23, 24) እርዳታ ለማግኘት ምንጊዜም ወደ ይሖዋ ጸልይ። ይሖዋ ኃያል በሆነው ቅዱስ መንፈሱ ተጠቅሞ እንደሚያጠነክርህና እንደሚደግፍህ እርግጠኛ ሁን። (1ጴጥ 5:10, 11) ይሖዋን ማገልገል ከሁሉ የተሻለ የሕይወት ጎዳና ነው። በመሆኑም እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ ስትል የምታደርገው ጥረት መቼም ቢሆን አያስቆጭህም!—መዝ 16:11

ወደ ጥምቀት የሚያደርሰው መንገድ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አንዳንዶች ለመጠመቅ ሲሉ የትኞቹን እንቅፋቶች መወጣት አስፈልጓቸዋል?

  • ራስህን ለይሖዋ ለመወሰን የሚያነሳሳ እምነት ለማዳበር ምን ሊረዳህ ይችላል?

  • አንዳንዶች ወደ ጥምቀት የሚያደርሱትን እርምጃዎች ለመውሰድ ያነሳሳቸው ምንድን ነው?

  • ይሖዋን ለማገልገል የሚመርጡ ሰዎች ምን በረከት ያገኛሉ?

  • ራስን ወስኖ መጠመቅ ምን ትርጉም አለው?

በጥምቀት ንግግሩ መደምደሚያ ላይ ተናጋሪው የጥምቀት ዕጩዎቹ ከተቀመጡበት እንዲነሱና ለሚከተሉት ሁለት ጥያቄዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው መልስ እንዲሰጡ ይጠይቃቸዋል፦

ከኃጢአታችሁ ንስሐ በመግባት፣ ራሳችሁን ለይሖዋ በመወሰንና ይሖዋ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያደረገውን የመዳን ዝግጅት በመቀበል ለመጠመቅ ዝግጁ ሆናችኋል?

መጠመቃችሁ በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ከታቀፉት የይሖዋ ምሥክሮች እንደ አንዱ እንደሚያስቆጥራችሁ ተገንዝባችኋል?

የጥምቀት ዕጩዎቹ ለእነዚህ ጥያቄዎች ‘አዎ’ የሚል መልስ መስጠታቸው በቤዛው ላይ እምነት እንዳላቸው የሚያሳይ ከመሆኑም ሌላ ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለይሖዋ መወሰናቸውን ‘በይፋ የሚናገሩበት’ አጋጣሚ ይሰጣቸዋል።—ሮም 10:9, 10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ