የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 ጥር ገጽ 13
  • ለሁሉም ሰው ለመስበክ መደራጀት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለሁሉም ሰው ለመስበክ መደራጀት
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ሌላ ቋንቋ ለሚናገር ሰው መመሥከር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • የውጭ አገር ቋንቋ ለሚናገሩ ሰዎች መስበክ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—በክልላችን ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በሙሉ ማነጋገር
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • የተለያዩ ቋንቋዎች በሚነገሩበት ክልል ውስጥ ተባብረን መስበክ የምንችለው እንዴት ነው?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 ጥር ገጽ 13
አንድ ወንድም ‘JW Language’ የተባለውን አፕሊኬሽን በታብሌቱ ላይ ሲጠቀም።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለሁሉም ሰው ለመስበክ መደራጀት

ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዳደራጃቸው ሁሉ በዛሬው ጊዜ ያሉ ሕዝቦቹንም ፈቃዱን እንዲያደርጉ አደራጅቷቸዋል። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች፣ ወረዳዎች፣ ጉባኤዎችና የመስክ አገልግሎት ቡድኖች የስብከቱን ሥራ ለማከናወን ተባብረው ይሠራሉ። ከእኛ የተለየ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችን ጨምሮ ለሁሉም ሰው እንሰብካለን።—ራእይ 14:6, 7

ሌሎችን ስለ እውነት ለማስተማር ስትል አዲስ ቋንቋ ለመማር አስበህ ታውቃለህ? አዲስ ቋንቋ ለመማር በቂ ጊዜ ባይኖርህም እንኳ JW Language በተባለው አፕሊኬሽን ተጠቅመህ ቀለል ያለ መግቢያ መማር ትችላለህ። ይህን መግቢያ በአገልግሎት ላይ ስትጠቀም በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት ክርስቲያኖች ያገኙትን ዓይነት ደስታ ማጣጣም ትችላለህ፤ እነዚህ ክርስቲያኖች ከሌሎች አገሮች የመጡ ሰዎች በየቋንቋቸው “ስለ አምላክ ታላቅ ሥራ” በመስማታቸው እጅግ ሲደነቁ ማየታቸው አስደስቷቸው ነበር።—ሥራ 2:7-11

የይሖዋ ወዳጅ ሁን—በውጭ አገር ቋንቋ መስበክ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘የይሖዋ ወዳጅ ሁን—በውጭ አገር ቋንቋ መስበክ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ካሌብ የእሱን ቋንቋ ለማትናገር ሴት ተርጓሚ ሮቦት ተጠቅሞ ሲሰብክ በሐሳቡ ሲታየው።

    JW Language የተባለው አፕሊኬሽን የሚጠቅምህ በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ነው?

  • ‘የይሖዋ ወዳጅ ሁን—በውጭ አገር ቋንቋ መስበክ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ‘በJW Language’ ላይ የሚገኘው ሰላምታንና መግቢያን የያዘው ገጽ።

    ይህ አፕሊኬሽን ካሉት ገጽታዎች መካከል አንዳንዶቹ የትኞቹ ናቸው?

  • ‘የይሖዋ ወዳጅ ሁን—በውጭ አገር ቋንቋ መስበክ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ካሌብና ሶፊያ ቀደም ሲል ሊያነጋግሯት የሞከሩት ሴት በቻይንኛ ሰላምታ ሲሰጧት በደስታ ስትቀበላቸው።

    ቋንቋቸው ምንም ይሁን ምን ለሁሉም ሰዎች ምሥራቹን መስበክ አለብን

    በክልላችሁ ውስጥ የትኞቹን ቋንቋዎች የሚናገሩ ሰዎች ይገኛሉ?

  • ሌላ ቋንቋ የሚናገር ሰው ለመንግሥቱ መልእክት ፍላጎት ካሳየ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?—od 100-101 አን. 39-41

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ