የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 ግንቦት ገጽ 7
  • ተግሣጽ የይሖዋ የፍቅር መግለጫ ነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተግሣጽ የይሖዋ የፍቅር መግለጫ ነው
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የተግሣጽን ዓላማ መረዳት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • ተግሣጽን የምትመለከተው እንዴት ነው?
    ወጣትነትህን በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት
  • ተግሣጽ—የአምላክ ፍቅር መግለጫ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • ለልጆቻችሁ ተግሣጽ መስጠት የሚኖርባችሁ እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 ግንቦት ገጽ 7
አንድ አባትና እናት፣ ለአካለ መጠን የደረሰ ልጃቸው ንስሐ ባለመግባቱ ቤታቸውን ለቆ ሲወጣ በራቸው ላይ ቆመው እያለቀሱ ያዩታል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ተግሣጽ የይሖዋ የፍቅር መግለጫ ነው

ተግሣጽ በአብዛኛው መመሪያና ትምህርት ከመስጠት ጋር ይያያዛል፤ ሆኖም እርማትንና ወቀሳን ሊያካትትም ይችላል። ይሖዋ ተግሣጽ የሚሰጠን እሱን ተቀባይነት ባለው መንገድ እንድናመልከው ሲል ነው። (ሮም 12:1፤ ዕብ 12:10, 11) አንዳንድ ጊዜ ተግሣጽ ሊያምም ይችላል፤ ሆኖም ጽድቅና በረከት ያስገኝልናል። (ምሳሌ 10:7) ታዲያ ተግሣጽ የሚሰጡም ሆነ የሚቀበሉ ሰዎች ምን ማስታወስ ይኖርባቸዋል?

ሰጪው። ሽማግሌዎች፣ ወላጆችም ሆኑ ሌሎች ተግሣጽ የሚሰጡት እንደ ይሖዋ በደግነትና በፍቅር ሊሆን ይገባል። (ኤር 46:28) ጠንከር ያለ ተግሣጽም ቢሆን ለሁኔታው የሚመጥን መሆን አለበት፤ ተግሣጹን የሚሰጡ ሰዎችም እንዲህ እንዲያደርጉ የሚያነሳሳቸው ፍቅር ሊሆን ይገባል።—ቲቶ 1:13

ተቀባዩ። ተግሣጽ የሚሰጠን በምንም መልክ ቢሆን ተግሣጹን ለመቀበል እንቢተኞች መሆን የለብንም፤ ከዚህ ይልቅ ተግሣጹን ተቀብለን በሥራ ላይ ለማዋል ፈጣኖች መሆን አለብን። (ምሳሌ 3:11, 12) ሁላችንም ፍጹማን ባለመሆናችን ተግሣጽ ያስፈልገናል፤ ተግሣጹ የሚመጣው በተለያየ መልክ ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከምናነበው ወይም በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ከምንሰማው ነገር ተግሣጽ ልናገኝ እንችላለን። ወይም ደግሞ አንዳንዶች በፍርድ ኮሚቴ ተግሣጽ ሊሰጣቸው ይችላል። ተግሣጽን መቀበል የኋላ ኋላ ሕይወት ያስገኛል።—ምሳሌ 10:17

“ይሖዋ የሚወዳቸውን ይገሥጻል” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘ይሖዋ የሚወዳቸውን ይገሥጻል’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ካነን ትንሽ ልጅ ሳለ ከወላጆቹ ጋር ሲሰብክ።

    የካነን የልጅነት ሕይወት ምን ይመስል ነበር? በኋላ የተቀየረውስ እንዴት ነው?

  • ‘ይሖዋ የሚወዳቸውን ይገሥጻል’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ሽማግሌዎች በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኘውን ካነንን ሲያነጋግሩት።

    ይሖዋ ምን ፍቅራዊ ተግሣጽ ሰጥቶታል?

  • ‘ይሖዋ የሚወዳቸውን ይገሥጻል’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። በጉልምስና ዕድሜ ላይ የሚገኘው ካነን በጉባኤ ስብሰባ ላይ ልጆችን ሲያነጋግር።

    ይሖዋ የሚሰጥህን ተግሣጽ በደስታ ተቀበል

    እሱ ካጋጠመው ነገር ምን እንማራለን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ