ክርስቲያናዊ ሕይወት
በቤተሰብ ውስጥ ፍቅር አሳዩ
ፍቅር እንደ ሙጫ ነው፤ አንድ ቤተሰብ የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖረው የማድረግ ኃይል አለው። ፍቅር ከሌለ የቤተሰቡ አባላት አንድነታቸውን መጠበቅና መተባበር ከባድ ይሆንባቸዋል። ታዲያ ባሎች፣ ሚስቶችና ወላጆች በቤተሰብ ውስጥ ፍቅር ማሳየት የሚችሉት እንዴት ነው?
አፍቃሪ የሆነ ባል የሚስቱን ፍላጎት፣ አመለካከትና ስሜት ግምት ውስጥ ያስገባል። (ኤፌ 5:28, 29) እንዲህ ዓይነቱ ባል፣ ቤተሰቡ በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ የሚያስፈልገውን ነገር ያቀርባል፤ ይህም ቋሚ የቤተሰብ አምልኮ ማድረግን ይጨምራል። (1ጢሞ 5:8) አፍቃሪ የሆነች ሚስት ለባሏ ትገዛለች፤ እንዲሁም ባሏን ‘በጥልቅ ታከብራለች።’ (ኤፌ 5:22, 33፤ 1ጴጥ 3:1-6) ባልም ሆነ ሚስት በነፃ ይቅር ለመባባል ፈቃደኞች መሆን አለባቸው። (ኤፌ 4:32) አፍቃሪ የሆኑ ወላጆች ለእያንዳንዱ ልጅ በግለሰብ ደረጃ ትኩረት ይሰጣሉ፤ እንዲሁም ልጆቻቸውን ይሖዋን እንዲወዱ ያስተምራሉ። (ዘዳ 6:6, 7፤ ኤፌ 6:4) ልጆቻቸው በትምህርት ቤት ምን ፈተና ያጋጥማቸዋል? የእኩዮች ተጽዕኖን በመቋቋም ረገድ እየተሳካላቸው ነው? በቤተሰብ ውስጥ ፍቅር ካለ ሁሉም የቤተሰቡ አባላት ተረጋግተው ያለስጋት መኖር ይችላሉ።
ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በቤተሰባችሁ ውስጥ አሳዩ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
አንድ አፍቃሪ ባል ሚስቱን የሚመግባትና የሚንከባከባት እንዴት ነው?
አንዲት አፍቃሪ ሚስት ለባሏ ጥልቅ አክብሮት የምታሳየው እንዴት ነው?
አፍቃሪ ወላጆች በልጆቻቸው ልብ ውስጥ የአምላክን ቃል መቅረጽ የሚችሉት እንዴት ነው?