የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 መስከረም ገጽ 5
  • የማስተዋል ችሎታችሁን አሠልጥኑ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የማስተዋል ችሎታችሁን አሠልጥኑ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥሩ ውሳኔ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • እምነት በማዳበር ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ አድርጉ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • አምላክን የሚያስከብር ውሳኔ አድርጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • መግቢያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2024
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 መስከረም ገጽ 5

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የማስተዋል ችሎታችሁን አሠልጥኑ

አንድ ስፖርተኛ ብቃቱን ይዞ ለመቀጠል ሁልጊዜ ልምምድ በማድረግ ጡንቻዎቹን ማሠራት አለበት። በተመሳሳይ እኛም፣ የማስተዋል ችሎታችንን ለማሠልጠንና ይህን ችሎታችንን ይዘን ለመቀጠል የማያቋርጥ ጥረት ማድረግ ያስፈልገናል። (ዕብ 5:14) እርግጥ ነው፣ ብዙ ጊዜ የሚቀናን የሌሎችን ውሳኔ አይተን በዚያ መሠረት መወሰን ሊሆን ይችላል፤ ይሁንና የማሰብ ችሎታችንን ማሠራትና የራሳችንን ውሳኔ ማድረግ ይኖርብናል። ለምን? ምክንያቱም እያንዳንዳችን ለምናደርገው ውሳኔ ለአምላክ መልስ እንሰጣለን።—ሮም 14:12

በእውነት ቤት ረጅም ዓመት ስለቆየን ብቻ ጥሩ ውሳኔ እንደምናደርግ ሊሰማን አይገባም። ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ ለማድረግ ከይሖዋ፣ ከቃሉና ከድርጅቱ በምናገኘው እርዳታ ሙሉ በሙሉ መጠቀም ይኖርብናል።—ኢያሱ 1:7, 8፤ ምሳሌ 3:5, 6፤ ማቴ 24:45

“ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • “ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ” ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ኤማና ባለቤቷ የሠርግ መጋበዣ ሲመለከቱ።

    ኤማ፣ ውሳኔ ማድረግ የሚጠይቅ ምን ሁኔታ አጋጥሟት ነበር?

  • “ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ” ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ኤሚ የራሷን አመለካከት በሌላ ላይ ለመጫን እየሞከረች እንዳለ በሚያሳይ መንገድ ስትናገር።

    ለሕሊና ከተተዉ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የራሳችንን አመለካከት በሌሎች ላይ መጫን የሌለብን ለምንድን ነው?

  • “ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ” ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ኤማ ሻርሌትን እና አለንን ምክር ስትጠይቅ።

    አንድ ባልና ሚስት ለኤማ ምን ጥሩ ምክር ሰጥተዋታል?

  • “ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ” ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ኤማ ኮምፒውተሯ ላይ “የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት” ተጠቅማ ምርምር ስታደርግ።

    ኤማ፣ ላለችበት ሁኔታ የሚሠራ ጠቃሚ መረጃ ያገኘችው ከየት ነው?

ውሳኔ ማድረግ ያለብኝ በምን ላይ ተመሥርቼ ነው?

  • በራሴ አመለካከት

  • በሌሎች አመለካከት

  • በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ