ክርስቲያናዊ ሕይወት
ከሳሙኤል ሕይወት የምናገኛቸው ትምህርቶች
ሳሙኤል እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ለይሖዋ ታማኝ ሆኗል። ልጅ በነበረበት ወቅት፣ ሆፍኒ እና ፊንሃስ የተባሉት የኤሊ ልጆች በሚያሳዩት ብልሹ ምግባር አልተሸነፈም። (1ሳሙ 2:22-26) ሳሙኤል እያደገ ሄደ፤ ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር። (1ሳሙ 3:19) ሳሙኤል በዕድሜ ከገፋ በኋላ፣ ልጆቹ ከይሖዋ ቢርቁም እሱ ለይሖዋ ታማኝ ሆኖ ቀጥሏል።—1ሳሙ 8:1-5
ሳሙኤል ከተወው ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? ልጆች ከሆናችሁ፣ ይሖዋ ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንደሚያጋጥሟችሁና ምን እንደሚሰማችሁ እንደሚያውቅ እርግጠኞች ሁኑ። ደፋር እንድትሆኑ ይረዳችኋል። (ኢሳ 41:10, 13) ወላጆች ከሆናችሁና ልጃችሁ ከይሖዋ ርቆ ከሆነ ከሳሙኤል ታሪክ መጽናኛ ማግኘት ትችላላችሁ፤ ሳሙኤል ለአካለ መጠን የደረሱ ልጆቹ የይሖዋን መሥፈርቶች እንዲያከብሩ ማስገደድ አልቻለም። ሳሙኤል ጉዳዩን ለይሖዋ ትቶታል፤ እሱ በግሉ ንጹሕ አቋሙን መጠበቁንና በሰማይ ያለውን አባቱን ይሖዋን ለማስደሰት ጥረት ማድረጉን ቀጥሏል። ምናልባት የእናንተ መልካም ምሳሌነት ልጃችሁ ወደ ይሖዋ እንዲመለስ ሊያነሳሳው ይችላል።
ከእነሱ ተማሩ—ሳሙኤል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ሳሙኤል ትንሽ ልጅ ሳለ ድፍረት ያሳየው እንዴት ነው?
ዳኒ ድፍረት ያሳየው እንዴት ነው?
ሳሙኤል በዕድሜ ከገፋ በኋላም ምን ግሩም ምሳሌ ትቷል?
ይሖዋ፣ ትክክል ለሆነው ነገር ቆራጥ አቋም ያላቸውን ሁሉ ይደግፋል
የዳኒ ወላጆች ምን ግሩም ምሳሌ ትተዋል?