ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ጥሩ ጓደኛ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?
ጓደኛችሁ የሚያስጨንቅ ነገር ሲያጋጥመው አጽናኑት እንዲሁም አበረታቱት (1ሳሙ 20:1, 2፤ w19.11 7 አን. 18)
ጓደኛችሁ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ከተሰማችሁ አስጠንቅቁት (1ሳሙ 20:12, 13፤ w08 2/15 8 አን. 7)
ሌሎች የጓደኛችሁን ስም ሲያጠፉት ለእሱ ጥብቅና ቁሙ (1ሳሙ 20:30-32፤ w09 10/15 19 አን. 11)
የይሖዋ ሕዝቦች ጥሩ ወዳጅነት መመሥረት የሚችሉባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሏቸው። ጓደኛ ለማግኘት እኛ ራሳችን ጥሩ ጓደኛ መሆን አለብን። በጉባኤህ ውስጥ ካሉት መካከል ከማን ጋር ጓደኛ መሆን ትፈልጋለህ?