የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb22 መጋቢት ገጽ 9
  • የኢንተርኔት ጓደኞችህ እነማን ናቸው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የኢንተርኔት ጓደኞችህ እነማን ናቸው?
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በኢንተርኔት ጓደኝነት ብመሠርት ምን ችግር አለው?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 2
  • ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀሙ ወጥመድ ውስጥ እንዳትገቡ ተጠንቀቁ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በተመለከተ ምን ማወቅ ይኖርብኛል?​—ክፍል 2
    ንቁ!—2011
  • ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ልጆች ወላጆች ማወቅ የሚገባቸው ነገር
    ንቁ!—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
mwb22 መጋቢት ገጽ 9

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የኢንተርኔት ጓደኞችህ እነማን ናቸው?

“ጓደኛ” የሚለው ቃል “በፍቅር ወይም በአክብሮት ተነሳስተን የምንቀርበው ሰው” የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል። ለምሳሌ ያህል፣ በዮናታን እና በዳዊት መካከል የማይበጠስ ወዳጅነት የተመሠረተው ዳዊት ጎልያድን ከገደለው በኋላ ነው። (1ሳሙ 18:1) ሁለቱም ሰዎች፣ አንዳቸውን በሌላው ዘንድ ተወዳጅ የሚያደርጋቸው ባሕርይ ነበራቸው። ስለዚህ የጠንካራ ወዳጅነት መሠረቱ ትክክለኛ እውቀት ነው። በጥቅሉ ሲታይ፣ አንድን ሰው ማወቅ ጊዜና ጥረት ይጠይቃል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ግን ሰዎች አንዲት ቁልፍ በመጫን ብቻ “ጓደኞች” መሆን ይችላሉ። ኢንተርኔት ላይ የምናገኛቸው ሰዎች፣ የሚናገሩትን ነገር በጥንቃቄ ማቀድና ሌሎች ለእነሱ የሚኖራቸውን አመለካከት በተወሰነ መጠን መቆጣጠር የሚችሉበት አጋጣሚ አላቸው፤ ይህም እውነተኛ ማንነታቸውን መደበቅ ቀላል እንዲሆንላቸው ያደርጋል። በመሆኑም በኢንተርኔት አማካኝነት ጓደኝነት ከመመሥረት ጋር በተያያዘ የምንመራበት መርሕ ሊኖረን ይገባል። ‘ስሜታቸውን ልጎዳው እችላለሁ’ ብላችሁ በማሰብ በደንብ የማታውቋቸው ሰዎች የሚያቀርቡላችሁን የጓደኝነት ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ አትፍሩ። አንዳንዶች ማኅበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም ያለውን አደጋ በመገንዘብ ጨርሶ ላለመጠቀም ወስነዋል። ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ለመጠቀም ከወሰናችሁ ግን ምን ነገሮችን ማስታወስ ይኖርባችኋል?

ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀም አስተዋይ ሁን የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • “ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀም አስተዋይ ሁን” ከሚለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። አንዲት ልጅ የቴሌቪዥን ስክሪን ላይ የሚታዩትን የራሷን ፎቶዎች በድንጋጤ ስትመለከት።

    አንድ ነገር ከመጻፍህ ወይም ፎቶዎችን ከመለጠፍህ በፊት ምን ነገሮችን ማስታወስ ይኖርብሃል?

  • ‘ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀም አስተዋይ ሁን’ ከሚለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ፊታቸው የሚያስፈራ ሁለት ወንዶች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተለጠፈን ነገር ለአንድ ልጅ ሲያሳዩት ልጁ ዓይኑን ሸፍኖ።

    ኢንተርኔት ላይ ጓደኛ የምታደርጋቸውን ሰዎች በጥንቃቄ መምረጥ ያለብህ ለምንድን ነው?

  • “ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀም አስተዋይ ሁን” ከሚለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ሌሊቱን ሙሉ ላፕቶፕ ሲጠቀም ያደረ አንድ ልጅ ላፕቶፑን ተደግፎ ተኝቷል።

    ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በመጠቀም በምታሳልፈው ጊዜ ላይ ገደብ ማበጀት ያለብህ ለምንድን ነው?—ኤፌ 5:15, 16

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ