የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb22 ግንቦት ገጽ 11
  • ምኞታችሁን ተቆጣጠሩት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምኞታችሁን ተቆጣጠሩት
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትንባሆ እና የኤሌክትሮኒክ ሲጋራ ስለማጨስ ምን ማወቅ ይኖርብኛል?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ከማጨስ ጋር በተያያዘ ምን ማወቅ ይኖርብኛል?
    ንቁ!—2011
  • ማጨስ በአምላክ ዘንድ እንዴት ይታያል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • መጥፎ ምኞቶችን ታግለህ ማሸነፍ የምትችለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2004
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
mwb22 ግንቦት ገጽ 11

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ምኞታችሁን ተቆጣጠሩ

ፍጹማን ያልሆንን ሰዎች እንደመሆናችን መጠን ምኞታችንን ለመቆጣጠር ያለማቋረጥ መታገል ይጠበቅብናል። ምኞታችንን ካልተቆጣጠርነው የይሖዋን ሞገስ ሊያሳጣን ይችላል። ለምሳሌ አንዳንዶች ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ ለማግኘት ያላቸው ምኞት ለአምላክ ካላቸው ፍቅር ሊበልጥባቸው ይችላል። ሌሎች ሰዎች ፆታዊ ምኞታቸውን ለማርካት ሲሉ የአምላክን መሥፈርቶች ይጥሳሉ። (ሮም 1:26, 27) ሌሎች ደግሞ ለመወደድ ወይም ተቀባይነት ለማግኘት ካላቸው ምኞት የተነሳ ለእኩዮች ተጽዕኖ እጅ ይሰጣሉ።—ዘፀ 23:2

ምኞታችንን መቆጣጠር የምንችለው እንዴት ነው? በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ለማተኮር አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል። (ማቴ 4:4) በተጨማሪም ይሖዋ ምኞታችንን ለመቆጣጠር እንዲረዳን ልንለምነው ይገባል። ለምን? ምክንያቱም ለእኛ ከሁሉ የተሻለውን የሚያውቀው እሱ ነው፤ እንዲሁም ተገቢ የሆኑ ፍላጎቶቻችንን እንዴት እንደሚያረካልን ያውቃል።—መዝ 145:16

ስታጨስ እንዳትጨስ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • “ስታጨስ እንዳትጨስ” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶ። አንድ ፋብሪካ የሚያጨሱ አሻንጉሊቶችን ሲሠራ።

    አንዳንዶች የሚያጨሱት ለምንድን ነው?

  • “ስታጨስ እንዳትጨስ” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶ። የአንድ አጫሽ ሳንባ በኃይል ሲያስል።

    ማጨስ ምን ጉዳት ያስከትላል?

  • “ስታጨስ እንዳትጨስ” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶ። አንድ ግዙፍ ነጋዴ የኤሌክትሮኒክ ሲጋራ በዓሣ ማጥመጃ ላይ አድርጎ ለአንዲት ወጣት ሴት ሲያቀርብላት።

    ትንባሆም ሆነ ኤሌክትሮኒክ ሲጋራ ማጨስ ስህተት የሆነው ለምንድን ነው?—2ቆሮ 7:1

  • “ስታጨስ እንዳትጨስ” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶ። አንዲት ወጣት ሰገነት ላይ ሆና የጠራውን ሰማይ ስትመለከት።

    የማጨስ ፍላጎትን ማሸነፍ ትችላለህ!

    ለማጨስ ስትፈተን ‘እንቢ’ ማለት ወይም ማጨስህን ማቆም የምትችለው እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ