የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb22 መስከረም ገጽ 5
  • ትዳር—የዕድሜ ልክ ጥምረት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትዳር—የዕድሜ ልክ ጥምረት
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ሳያገቡ ስለመኖርና ስለ ትዳር ምን ይላል?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ጋብቻ​—አፍቃሪ ከሆነው አምላክ የተገኘ ስጦታ
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • የተሳካ ትዳር ለመመሥረት መዘጋጀት
    ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
  • ጋብቻ—ከአምላክ የተገኘ ስጦታ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
mwb22 መስከረም ገጽ 5
አንድ ባልና ሚስት አብረው ሲያገለግሉ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ትዳር—የዕድሜ ልክ ጥምረት

ስኬታማ ትዳር ይሖዋን ያስከብራል፤ ለባልና ሚስቱም ደስታ ያስገኛል። (ማር 10:9) ክርስቲያኖች ዘላቂና ደስተኛ ትዳር መመሥረት ከፈለጉ የትዳር ጓደኛቸውን ሲመርጡ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን በጥብቅ መከተል ይኖርባቸዋል።

“አፍላ የጉርምስና ዕድሜ” ሳያልፍ መጠናናት አለመጀመር ጥበብ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ ዕድሜ ላይ የፆታ ስሜት ስለሚያይል ጥሩ ውሳኔ የማድረግ ችሎታን ሊያዛባ ይችላል። (1ቆሮ 7:36) በነጠላነት የምትቆዩበትን ጊዜ በጥበብ ተጠቀሙበት፤ ከአምላክ ጋር ያላችሁን ዝምድና ለማጠናከርና ክርስቲያናዊ ባሕርያትን ለማዳበር ጥረት አድርጉ። ይህም በኋላ ላይ ትዳር ሲመጣ ጥሩ አጋር እንድትሆኑ ያስችላችኋል።

አንድን ሰው ለማግባት ከመወሰናችሁ በፊት ጊዜ ወስዳችሁ የግለሰቡን “የተሰወረ የልብ ሰው” ለማወቅ ጥረት አድርጉ። (1ጴጥ 3:4) ጥርጣሬ የሚፈጥርባችሁ ከበድ ያለ ነገር ካስተዋላችሁ ልታገቡት ላሰባችሁት ሰው አንሱለት። እንደ ማንኛውም ማኅበራዊ ግንኙነት ሁሉ ትዳር ላይም ቅድሚያ የሚሰጠው ‘ምን አገኛለሁ’ የሚለው ሳይሆን ‘ምን እሰጣለሁ’ የሚለው እንደሆነ አትርሱ። (ፊልጵ 2:3, 4) ከትዳር በፊት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ ለደስተኛ ትዳር መሠረት መጣል ትችላላችሁ።

ለጋብቻ መዘጋጀት—ክፍል 3፦ ‘ወጪያችሁን አስሉ’ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • እህታችንና ሼን መጀመሪያ ላይ የነበራቸው ግንኙነት ምን ይመስላል?

  • ጊዜ እያለፈ ሲሄድ እህት ምን አስተዋለች?

  • ወላጆቿ የረዷት እንዴት ነው? ምን ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔስ አድርጋለች?

እየተጠናናህ ያለህ ወንድም ነህ? እስቲ እነዚህን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

ምን ግሩም ክርስቲያናዊ ባሕርያት አሏት? መንግሥቱን እንደምታስቀድም እያሳየች ያለችው እንዴት ነው? ለቲኦክራሲያዊ መመሪያ አክብሮት አላት? ለሌሎች አሳቢ እንደሆነች በግልጽ ይታያል?

እየተጠናናሽ ያለሽ እህት ነሽ? እስቲ እነዚህን ጥያቄዎች አስቢባቸው፦

ምን ግሩም ክርስቲያናዊ ባሕርያት አሉት? ከሥራው፣ ከገንዘብ፣ ከስፖርት ወይም ከመዝናኛ ይልቅ ለአምልኮውና ለጉባኤ ኃላፊነቶቹ ቅድሚያ ይሰጣል? ቤተሰቡን የሚይዘው እንዴት ነው? ለሌሎች አሳቢ እንደሆነ በግልጽ ይታያል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ