ክርስቲያናዊ ሕይወት
በትንሣኤ እስክንገናኝ ድረስ
የምንወደው ሰው ሲሞት የትንሣኤ ተስፋ ያጽናናናል። እንደዚያም ሆኖ ኃጢአትና ሞት እንደ ከፈን ሁላችንንም አላፈናፍን ብለውናል። (ኢሳ 25:7, 8) “ፍጥረት ሁሉ . . . አብሮ በመቃተትና በመሠቃየት ላይ” የሚገኝበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው። (ሮም 8:22) በሞት ያጣነውን ሰው ዳግም እስክናገኘው ድረስ ሐዘኑን ለመቋቋም ምን ይረዳናል? የአምላክ ቃል ጠቃሚ ሐሳቦች ያካፍለናል።
የምትወዱት ሰው ሲሞት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ዳኒዬል እንዲሁም ማሳሂሮ እና ዮሺሚ ምን ሐዘን ደርሶባቸዋል?
የረዷቸው አምስት ተግባራዊ ምክሮች የትኞቹ ናቸው?
የላቀ ማጽናኛ የሚገኘው ከማን ነው?—2ቆሮ 1:3, 4