ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ ፈተናዎችን እንድንወጣ ይረዳናል
በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት በርካታ ከባባድ ፈተናዎች ያጋጥሙናል። አንዳንድ ጊዜ ያጋጠሙን ፈተናዎች ከአቅማችን በላይ እንደሆኑ ይሰማን ይሆናል። ይሁንና ወደ ይሖዋ መቅረባችንን ከቀጠልን እሱ ቅስም የሚሰብሩ ፈተናዎችን እንኳ እንድንወጣ ይረዳናል። (ኢሳ 43:2, 4) ታዲያ በፈተና ውስጥ ሆነንም ወደ ይሖዋ መቅረብ የምንችለው እንዴት ነው?
ጸሎት። ልባችንን በይሖዋ ፊት ስናፈስ እሱ ለመጽናት የሚያስችል የአእምሮ ሰላምና የመንፈስ ጥንካሬ ይሰጠናል።—ፊልጵ 4:6, 7፤ 1ተሰ 5:17
ስብሰባ። ይሖዋ በስብሰባዎች አማካኝነት የሚሰጠን መንፈሳዊ ምግብና ከወንድሞቻችን የምናገኘው ማበረታቻ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ያስፈልገናል። (ዕብ 10:24, 25) ለስብሰባዎች ስንዘጋጅ፣ በስብሰባዎች ላይ ስንገኝ እንዲሁም ሐሳብ ስንሰጥ ይሖዋ በመንፈሱ አማካኝነት ከሚሰጠው እርዳታ ሙሉ ጥቅም ማግኘት እንችላለን።—ራእይ 2:29
አገልግሎት። አቅማችን በፈቀደ መጠን በአገልግሎት ላይ የተሟላ ተሳትፎ ስናደርግ አዎንታዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ማተኮር ይበልጥ ቀላል ይሆንልናል። ከዚህም ሌላ፣ ከይሖዋና አብረውን ከሚሠሩት ሰዎች ጋር ያለን ወዳጅነት እየተጠናከረ ይሄዳል።—1ቆሮ 3:5-10
ይሖዋ ይቀበላችኋል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ማሉ ፈተና ባጋጠማት ወቅት ወደ ይሖዋ እንድትቀርብ የረዳት ምንድን ነው?
ልክ እንደ ማሉ በመዝሙር 34:18 ላይ የሚገኘው ሐሳብ በፈተና ወቅት የሚያጽናናን እንዴት ነው?
የማሉ ተሞክሮ ይሖዋ በፈተና ወቅት ‘ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነውን ኃይል’ እንደሚሰጠን የሚያሳየው እንዴት ነው?—2ቆሮ 4:7