የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp21 ቁጥር 1 ገጽ 10-13
  • አምላክ ጸሎትህን እንዲሰማ እንዴት መጸለይ ይኖርብሃል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ጸሎትህን እንዲሰማ እንዴት መጸለይ ይኖርብሃል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በኢየሱስ ስም ወደ ይሖዋ አምላክ ጸልይ
  • የልብህን አውጥተህ ተናገር
  • ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ጸልይ
  • ስለ የትኞቹ ነገሮች መጸለይ እንችላለን?
  • በትዕግሥት መጸለይህን ቀጥል
  • በጸሎት አማካኝነት ወደ አምላክ ቅረብ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር መቀራረብ
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
wp21 ቁጥር 1 ገጽ 10-13

አምላክ ጸሎትህን እንዲሰማ እንዴት መጸለይ ይኖርብሃል?

ይሖዋ “ጸሎት ሰሚ” አምላክ ነው። (መዝሙር 65:2) በማንኛውም ሰዓትና ቦታ በልባችንም ሆነ ጮክ ብለን እሱን ማነጋገር እንችላለን። ይሖዋ፣ ‘አባት’ ብለን እንድንጠራው ይፈልጋል፤ ደግሞም ከእሱ የተሻለ አባት ልናገኝ አንችልም። (ማቴዎስ 6:9) ይሖዋ ስለሚወደን ጸሎታችን ተሰሚነት እንዲያገኝ ከፈለግን እንዴት መጸለይ እንዳለብን ያስተምረናል።

በኢየሱስ ስም ወደ ይሖዋ አምላክ ጸልይ

“አብን ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትጠይቁት ይሰጣችኋል።”​—ዮሐንስ 16:23

ኢየሱስ የተናገራቸው ቃላት ይሖዋ በምስሎች፣ በቅዱሳን፣ በመላእክት ወይም በሞቱ ሰዎች በኩል ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወደ እሱ እንድንጸልይ እንደሚፈልግ በግልጽ ያሳያሉ። በኢየሱስ ስም ወደ አምላክ ስንጸልይ ኢየሱስ የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና እንደተገነዘብን እናሳያለን። ኢየሱስ “በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” በማለት ተናግሯል።—ዮሐንስ 14:6

የልብህን አውጥተህ ተናገር

“ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ።”​—መዝሙር 62:8

ወደ ይሖዋ ስንጸልይ አፍቃሪ የሆነን አባት በምናነጋግርበት መንገድ ልናነጋግረው ይገባል። የተጻፈ ነገር እያነበብን ወይም የተሸመደደ ነገር እየደገምን ከመጸለይ ይልቅ በአክብሮት የልባችንን አውጥተን ለአምላክ መንገር ይኖርብናል።

ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ጸልይ

“የምንጠይቀው ነገር ምንም ይሁን ምን ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ እስከለመንን ድረስ ይሰማናል።”​—1 ዮሐንስ 5:14

ይሖዋ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እሱ ለእኛ የሚያደርጋቸውን ነገሮችና እኛ እንድናደርግ የሚፈልጋቸውን ነገሮች አሳውቆናል። ጸሎታችን በአምላክ ዘንድ ተሰሚነት እንዲያገኝ ከፈለግን “ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ” መለመን ይኖርብናል። ይህን ማድረግ እንድንችል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት እሱን በሚገባ ማወቅ ያስፈልገናል። እንዲህ ማድረጋችን አምላክን የሚያስደስት ጸሎት ለማቅረብ ያስችለናል።

ስለ የትኞቹ ነገሮች መጸለይ እንችላለን?

አንድ ቤተሰብ ከመመገቡ በፊት አብሮ ሲጸልይ

የሚያስፈልጉህን ነገሮች ለማግኘት ጸልይ። አምላክ እንደ ምግብ፣ ልብስና መጠለያ ያሉ መሠረታዊ ፍላጎቶቻችንን እንዲያሟላልን ልንጸልይ እንችላለን። በተጨማሪም ትክክለኛ ውሳኔ ለማድረግ የሚያስችል ጥበብና ፈተናዎችን ለመቋቋም የሚያስችል ጥንካሬ ለማግኘት መጸለይ እንችላለን። አምላክ እምነት እንዲጨምርልን፣ ኃጢአታችንን ይቅር እንዲለንና እንዲረዳን መጸለያችንም አስፈላጊ ነው።—ሉቃስ 11:3, 4, 13፤ ያዕቆብ 1:5, 17

አንድ ባል በሆስፒታል አልጋ ላይ ከተኛች ሚስቱ ጋር አብሮ ሲጸልይ

ስለ ሌሎች ሰዎች ጸልይ። አፍቃሪ ወላጆች ልጆቻቸው እርስ በርስ ሲዋደዱ ደስ ይላቸዋል። ይሖዋም በምድር ላይ ያሉ ልጆቹ እርስ በርስ እንዲተሳሰቡ ይፈልጋል። ከዚህ አንጻር ለትዳር ጓደኛችን፣ ለልጆቻችን፣ ለቤተሰባችንና ለወዳጆቻችን መጸለይ ተገቢ ነው። ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ “አንዳችሁ ለሌላው ጸልዩ” ብሏል።—ያዕቆብ 5:16

አንድ ሰው አመሻሹ አካባቢ ሜዳ ላይ ሲሄድ

ምስጋናህን ግለጽ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፈጣሪያችን ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “ከሰማይ ዝናብ በማዝነብና ፍሬያማ ወቅቶችን በመስጠት እንዲሁም የተትረፈረፈ ምግብ በማቅረብና ልባችሁን በደስታ በመሙላት መልካም ነገር አድርጓል።” (የሐዋርያት ሥራ 14:17) አምላክ ስላደረገልን በርካታ ነገሮች ስናስብ እሱን በጸሎት ለማመስገን እንነሳሳለን። እርግጥ ነው፣ ለአምላክ ያለንን አመስጋኝነት በአኗኗራችንም ልናሳይ ይገባል።—ቆላስይስ 3:15

በትዕግሥት መጸለይህን ቀጥል

አንዳንድ ጊዜ፣ ላቀረብነው ከልብ የመነጨ ጸሎት ቶሎ ምላሽ ባለማግኘታችን ልናዝን እንችላለን። ታዲያ በዚህ ጊዜ አምላክ ለእኛ ግድ እንደሌለው ልናስብ ይገባል? በፍጹም! ቀጥሎ የተጠቀሱት ተሞክሮዎች መጸለያችንን መቀጠላችን አስፈላጊ መሆኑን ያሳያሉ።

በመጀመሪያው ርዕስ ላይ የተጠቀሰው ስቲቭ “ወደ አምላክ ባልጸልይ ኖሮ ገና ድሮ በሕይወቴ ተስፋ እቆርጥ ነበር” በማለት ተናግሯል። ስቲቭ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱና ሳይታክቱ የመጸለይን አስፈላጊነት መማሩ ለውጥ እንዲያደርግ ረድቶታል። እንዲህ ብሏል፦ “ውድ ወዳጆቼ ላሳዩኝ ፍቅርና ድጋፍ ሁሉ አምላክን በጸሎት አመሰግነዋለሁ። አሁን ከምንጊዜውም ይበልጥ ደስተኛ ነኝ።”

አምላክ ጸሎቴን ይሰማል ብላ መጠበቅ እንደሌለባት ታስብ የነበረችውን የጄኒን ተሞክሮም እንመልከት። “ዋጋ ቢስ እንደሆንኩ የሚሰማኝ ስሜት በጣም ያየለበት ወቅት ነበር፤ በዚህ ወቅት፣ እንዲህ የሚሰማኝ ለምን እንደሆነ መገንዘብ እንድችል እንዲረዳኝ አምላክን ለመንኩት” ብላለች። እንዲህ ማድረጓ የረዳት እንዴት ነው? እንዲህ ብላለች፦ “የሚሰማኝን ስሜት ለአምላክ መናገሬ ለራሴ ሚዛናዊ አመለካከት እንድይዝ ረድቶኛል። ልቤ ቢኮንነኝም አምላክ ግን እንደማይኮንነኝ እንዳስተውል አድርጎኛል። በተጨማሪም ተስፋ እንዳልቆርጥ ብርታት ሰጥቶኛል።” አክላም እንዲህ ብላለች፦ “ጸሎት ይሖዋ እውን እንዲሆንልኝና እሱን እንደ አፍቃሪ አምላክ፣ አባትና ወዳጅ እንድመለከተው ረድቶኛል። እሱ የሚፈልገውን ነገር ለማድረግ እስከጣርኩ ድረስ ሁሌም ከጎኔ ሆኖ ይረዳኛል።”

ኢሳቤል ከባለቤቷና ከልጇ ጋር

ኢሳቤል ልጇ ጄራርድ የአካል ጉዳት እያለበትም በሕይወቱ ደስተኛ እንደሆነ ስትመለከት “አምላክ ከሁሉ በተሻለ መንገድ ጸሎቴን እንደመለሰልኝ ይሰማኛል” ብላለች

ኢሳቤል የተባለች ሴት ያጋጠማትን ሁኔታም እንመልከት። እርጉዝ ሳለች ሐኪሞቿ ልጇ ከባድ እክል ይዞ እንደሚወለድ ነገሯት። ኢሳቤል ይህን ስትሰማ በጣም አዘነች። በወቅቱ አንዳንዶች ጽንሱን እንድታስወርድ መክረዋት ነበር። ኢሳቤል “በጣም ከመጨነቄ የተነሳ የምሞት መስሎኝ ነበር” ብላለች። ታዲያ በዚህ ጊዜ ምን አደረገች? “አምላክ እንዲረዳኝ በተደጋጋሚ ጸለይኩ” ብላለች። ከጊዜ በኋላ ጄራርድ የተባለ ልጅ የወለደች ሲሆን ልጁ የአካል ጉዳት ነበረበት። ኢሳቤል አምላክ ጸሎቷን እንደመለሰላት ይሰማታል? አዎ። በምን መንገድ? ኢሳቤል እንዲህ ብላለች፦ “አሁን 14 ዓመት የሆነው ልጄ የአካል ጉዳት እያለበትም በሕይወቱ ደስተኛ እንደሆነ ስመለከት አምላክ ከሁሉ በተሻለ መንገድ ጸሎቴን እንደመለሰልኝ ይሰማኛል። ልጄ ከይሖዋ አምላክ ያገኘሁት ከሁሉ የላቀ በረከት ነው።”

እንዲህ ያሉ ከልብ የመነጩ አገላለጾች መዝሙራዊው የተናገረውን የሚከተለውን ሐሳብ ያስታውሱናል፦ “ይሖዋ ሆይ፣ የዋሆች የሚያቀርቡትን ልመና . . . ትሰማለህ። ልባቸውን ታጸናለህ፤ ደግሞም ትኩረት ትሰጣቸዋለህ።” (መዝሙር 10:17) በእርግጥም ሳናቋርጥ እንድንጸልይ የሚያነሳሱን አጥጋቢ ምክንያቶች አሉን!

ኢየሱስ ያቀረባቸው በርካታ ጸሎቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል በስፋት የሚታወቀው ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማራቸው ጸሎት ነው። ከዚህ ጸሎት ምን እንማራለን?

ኢየሱስ ያስተማረው የጸሎት ናሙና

ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ተራራ ላይ ሲሰብክ በትኩረት ሲያዳምጡ

ኢየሱስ በተራራው ስብከት ላይ ለደቀ መዛሙርቱ እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው አስተምሯቸዋል፤ ይህ ጸሎት በአብዛኛው የጌታ ጸሎት ወይም አቡነ ዘበሰማያት ተብሎ ይታወቃል። (ማቴዎስ 6:9-13፤ በተጨማሪም ሉቃስ 11:2-4⁠ን ተመልከት።) ባለፉት መቶ ዘመናት ይህ ጸሎት በስፋት ከመታወቁ የተነሳ ብዙዎች በቃላቸው ሸምድደው ይደግሙታል። ሆኖም ኢየሱስ ይህን ጸሎት ያስተማረበት ዓላማ ይህ ነበር? እንዳልሆነ ግልጽ ነው፤ ምክንያቱም ቀደም ሲል ኢየሱስ በዚያው ስብከት ላይ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት ከመደጋገም እንዲቆጠቡ ነግሯቸዋል። (ማቴዎስ 6:7) ኢየሱስ ይህን ጸሎት ያስተማረው ተከታዮቹ እንዴትና ስለ የትኞቹ ነገሮች መጸለይ እንዳለባቸው እንዲያውቁ ለመርዳት ነው። ከዚህ ጸሎት የምናገኘውን ትምህርት እስቲ እንመልከት።

“በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ”

  • መጸለይ ያለብን ወደ አምላክ ብቻ ነው።

“ስምህ ይቀደስ”

  • ይሖዋ የሚለው የአምላክ ስም ሊከበርና ቅዱስ ተደርጎ ሊታይ ይገባዋል።

“መንግሥትህ ይምጣ”

  • የአምላክ መንግሥት በሰማይ ያለ መስተዳድር ሲሆን ንጉሡም ኢየሱስ ነው። በቅርቡም መላዋን ምድር መግዛት ይጀምራል።

“ፈቃድህ በሰማይ እየተፈጸመ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይፈጸም”

  • አምላክ ለሰው ልጆች ያለው ፈቃድ ለዘላለም በምድር ላይ በሰላም እንዲኖሩ ነው።

“የዕለቱን ምግባችንን ዛሬ ስጠን”

  • በሕይወት ለመቀጠል የሚያስፈልጉንን ነገሮች የሚያሟላልን ይሖዋ ነው።

“በደላችንን ይቅር በለን”

  • ሁላችንም ብዙ ስህተት ስለምንሠራ የአምላክን ይቅርታ ማግኘት ያስፈልገናል።

እነዚህን ነጥቦች ማስታወስህ በደንብ የታሰበበት ጸሎት እንድታቀርብ ይረዳሃል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ