የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp21 ቁጥር 2 ገጽ 10-12
  • መጪው አዲስ ዓለም ውስጥ ለመኖር ምን ማድረግ ትችላለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጪው አዲስ ዓለም ውስጥ ለመኖር ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክን ‘በማወቅ’ ከመጪው ጥፋት መትረፍ ትችላለህ
  • የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብብ
  • አምላክ እንዲረዳህ ጸልይ
  • አምላክ ከዚህ በፊት ምን አድርጓል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • ለዘላለም መኖር የምትችለው እንዴት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • አምላክ በሚያመጣው ሰላማዊ አዲስ ዓለም ውስጥ መኖር ትችላለህ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ከመቃብር ወጥቶ እንደገና መኖር ይቻላል!
    ንቁ!—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
wp21 ቁጥር 2 ገጽ 10-12

መጪው አዲስ ዓለም ውስጥ ለመኖር ምን ማድረግ ትችላለህ?

ቀደም ባሉት ርዕሶች ላይ እንዳየነው፣ በቅርቡ አምላክ ይህን ክፉ ሥርዓት ከነችግሮቹ ጠራርጎ ያጠፋዋል። ይህ እንደሚሆን ምንም አንጠራጠርም። ለምን? ምክንያቱም የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ቃል ገብቶልናል፦

“ዓለምም ሆነ ምኞቱ ያልፋሉ።”—1 ዮሐንስ 2:17

ከጥፋቱ የሚተርፉ ሰዎች እንደሚኖሩም እርግጠኞች ነን፤ ምክንያቱም ከላይ ያለው ጥቅስ እንዲህ የሚል ሐሳብም ይዟል፦

“የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።”

ስለዚህ ከጥፋቱ ለመትረፍ የአምላክን ፈቃድ ማድረግ አለብን። የአምላክ ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በመጀመሪያ እሱን ማወቅ ያስፈልጋል።

አምላክን ‘በማወቅ’ ከመጪው ጥፋት መትረፍ ትችላለህ

ፎቶግራፎች፦ 1. አንዲት ነርስ ሆስፒታል ውስጥ ወለሉ ላይ ቁጭ ብላለች፤ የድካም የውጥረት ስሜት ይታይባታል። 2. ካፍቴሪያው ውስጥ አረፍ ብላለች፤ አንዲት የሥራ ባልደረባዋ በደስታ አንድ መጽሔት ስታነብ ትመለከታለች። 3. የሥራ ባልደረባዋ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድ ጥቅስ አነበበችላት፤ ከዚያም የjw.org የአድራሻ ካርድ ሰጠቻት።

ኢየሱስ “ብቸኛው እውነተኛ አምላክ የሆንከውን አንተን . . . ማወቅ የዘላለም ሕይወት ነው” ብሏል። (ዮሐንስ 17:3) ከመጪው ጥፋት ለመትረፍና ለዘላለም ለመኖር አምላክን “ማወቅ” ያስፈልገናል። ይህ ሲባል እንዲሁ አምላክ እንዳለ አምኖ መቀበል ወይም ስለ እሱ አንዳንድ ነገሮችን ማወቅ ማለት ብቻ አይደለም። ከእሱ ጋር ወዳጅነት መመሥረት ያስፈልጋል። ከአንድ ሰው ጋር ጥሩ ወዳጅነት መመሥረት የምንችለው አብረን ጊዜ ስናሳልፍ ነው። ከአምላክ ጋር ወዳጅነት ለመመሥረትም እንዲሁ ማድረግ አለብን። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን እውነቶች መማራችን ከአምላክ ጋር ጥሩ ወዳጅነት ለመመሥረት ይረዳናል፤ እስቲ ከእነዚህ እውነቶች አንዳንዶቹን እንመልከት።

ከመጽሐፍ ቅዱስ የትኞቹን እውነቶች እንማራለን?

ነርሷ ቤቷ ሆና jw.org የተባለውን ድረ ገጽ ስትቃኝ።

አምላክ የሰው ልጆችን የፈጠረው ገነት ውስጥ እንዲኖሩ እንደሆነ እንማራለን።

የመጀመሪያዎቹን ሰዎች ማለትም አዳምን እና ሔዋንን ከፈጠረ በኋላ የኤደን ገነት ተብሎ በሚጠራ ውብ ቦታ አስቀመጣቸው። አዳምና ሔዋን ፍጹም ነበሩ፤ አምላክም ደስተኛ ሆነው እንዲኖሩ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ አሟልቶላቸዋል። ለዘላለም መኖር ይችሉ ነበር። ከአምላክ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት የሚያሳጣ ነገር እስካላደረጉ ድረስ ፈጽሞ አይሞቱም ነበር። እነሱ ግን አምላክ የሰጣቸውን ቀላል ትእዛዝ ሆን ብለው ጣሱ።

አሁን ችግርና መከራ የሚደርስብን ለምን እንደሆነ እንማራለን።

የመጀመሪያው ሰው አዳም፣ የአምላክን ትእዛዝ ሲጥስ ለዘላለም የመኖር አጋጣሚውን አጣ፤ ዘሮቹም ይህ አጋጣሚ እንዲያመልጣቸው አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ ጉዳዩን ሲያብራራ እንዲህ ይላል፦ “በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ . . . ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።” (ሮም 5:12) ከወላጅ ወደ ልጅ እንደሚተላለፍ የጤና እክል ሁሉ የአዳም ልጆችም ከእሱ ኃጢአትን ወርሰዋል። የምናረጀውና የምንሞተው ለዚህ ነው።

አምላክ እኛን ለመርዳት ምን እርምጃ እንደወሰደ እንማራለን።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል።” (ዮሐንስ 3:16) አምላክ ኢየሱስን ወደ ምድር በመላክ ለእኛ ሲል እንዲሞት አድርጓል። ፕራባካር የተባሉ የ86 ዓመት ሕንዳዊ፣ አምላክ በዚህ መንገድ ስላሳየን ፍቅር ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፦ “ይሖዋa ምን ያህል እንደሚወደኝ የሚያሳይ ነው። ለዘላለም የመኖር ተስፋ እንዲኖረኝ ያደረገው ፍቅሩ ነው።”

አምላክ ላደረገልን ነገር አድናቆታችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንማራለን።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ላደረገልን ነገር አድናቆታችንን ማሳየት የምንችልበት አንዱ መንገድ ‘ትእዛዛቱን መፈጸም’ እንደሆነ ይናገራል። (1 ዮሐንስ 2:3) ይሖዋ አምላክ ስለሚወደን አሁን ደስተኛ ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለብን ነግሮናል። (ኢሳይያስ 48:17, 18 የግርጌ ማስታወሻ) አምላክ ችግር ውስጥ እንድንገባ አይፈልግም። እሱን ከታዘዝነው አሁን ደስተኛ ሕይወት እንደሚኖረን፣ ወደፊት ደግሞ የዘላለም ሕይወት እንደሚሰጠን ቃል ገብቶልናል።

የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብብ

ነርሷ በምሳ እረፍቷ ወቅት ውጭ ሆና መጽሐፍ ቅዱስ እያነበበች ነው፤ ቀና ብላ ወደ ሰማይ ትመለከታለች።

አምላክ እንዲረዳህ የምትጸልይና የእሱን ፈቃድ የምታደርግ ከሆነ በዓለም ላይ ከሚመጣው ጥፋት መትረፍ ትችላለህ

በሕይወት ለመኖር ዘወትር መመገብ ያስፈልገናል። ሆኖም ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “ሰው ከይሖዋ አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ አይኖርም።”—ማቴዎስ 4:4

በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ቃል የምናገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። ይህን ቅዱስ መጽሐፍ ስታጠና አምላክ ባለፉት ዘመናት ለሰው ልጆች ምን እንዳደረገ፣ አሁን ምን እያደረገልን እንደሆነና ወደፊት ምን እንደሚያደርግልን ትረዳለህ።

አምላክ እንዲረዳህ ጸልይ

የአምላክን መመሪያ መታዘዝ ብትፈልግም እሱ ስህተት ናቸው ያላቸውን ነገሮች መተው ከብዶሃል? ታዲያ ምን ማድረግ ትችላለህ? አምላክን በደንብ ማወቅህ በዚህ ረገድ በጣም ይጠቅምሃል።

እስቲ ሳኩራb የተባለችን ሴት ሁኔታ እንደ ምሳሌ እንመልከት፤ ይህች ሴት መጥፎ ሥነ ምግባር የነበራት ሴት ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስትጀምር አምላክ “ከፆታ ብልግና ሽሹ” የሚል ትእዛዝ እንደሰጠ ተረዳች። (1 ቆሮንቶስ 6:18) ሳኩራ አምላክ ኃይል እንዲሰጣት በመጸለይ ይህን መጥፎ ልማዷን ማቆም ቻለች። ይሁንና አሁንም መጥፎ ልማዷ እንዳያገረሽባት መታገል ያስፈልጋታል። እንዲህ ብላለች፦ “መጥፎ ሐሳቦች ወደ አእምሮዬ ሲመጡ በጸሎት ለይሖዋ በግልጽ እነግረዋለሁ፤ ምክንያቱም በራሴ ኃይል ታግዬ ማሸነፍ እንደማልችል አውቃለሁ። ጸሎት ያለውን ኃይል መመልከቴ ከይሖዋ ጋር ያለኝ ወዳጅነት እንዲጠናከር ረድቶኛል።” እንደ ሳኩራ ሁሉ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎችም ከአምላክ ጋር ወዳጅነት መመሥረት ችለዋል። አምላክ አካሄዳቸውን አስተካክለው እሱን በሚያስደስት መንገድ ሕይወታቸውን መምራት እንዲችሉ ኃይል ሰጥቷቸዋል።—ፊልጵስዩስ 4:13

አምላክን ይበልጥ እያወቅከው ስትሄድ እሱም አንተን ‘ያውቅሃል’፤ እንደ ወዳጁ አድርጎ ይመለከትሃል። (ገላትያ 4:9፤ መዝሙር 25:14) ይህ ደግሞ ከመጪው ጥፋት ለመትረፍና አምላክ ባዘጋጀው አዲስ ዓለም ውስጥ ለመኖር ያስችልሃል። ይሁንና መጪው አዲስ ዓለም ውስጥ ሕይወት ምን ይመስላል? ቀጣዩ ርዕስ ይህን ያብራራል።

a መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአምላክ ስም ይሖዋ ነው።

b ስሟ ተቀይሯል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ