የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w22 ሰኔ ገጽ 29
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ጌታ በእውነት ተነሥቶአል”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ባዶ መቃብር—ኢየሱስ ሕያው ሆነ!
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ኢየሱስ ሕያው ሆነ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
w22 ሰኔ ገጽ 29

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ሮማውያን እንደ ኢየሱስ ያለ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ የተገደለ ሰው በሥርዓት እንዲቀበር ይፈቅዱ ነበር?

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አስከሬኑን ከመከራ እንጨቱ አውርደው በጨርቅ ሲጠቀልሉት።

ኢየሱስ በሁለት ወንጀለኞች መሃል በእንጨት ላይ ተሰቅሎ እንደተገደለ የሚገልጸውን ታሪክ ብዙዎች ያውቁታል። (ማቴ. 27:35-38) ሆኖም ኢየሱስ ከተሰቀለ በኋላ አስከሬኑን ለቀብር አዘጋጅተው በመቃብር ውስጥ እንዳኖሩት የሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ትክክል እንዳልሆነ የሚሰማቸው ሰዎች አሉ።—ማር. 15:42-46

የወንጌል ዘገባዎችን የሚተቹ አንዳንድ ሰዎች፣ ሞት ተፈርዶበት የተገደለ ሰው በመቃብር ውስጥ በሥርዓት ሊቀበር እንደማይችል ያምኑ ነበር። ከዚህ ይልቅ የተገደሉ ወንጀለኞች አስከሬናቸው በተለየ መንገድ እንደሚያዝ ይሰማቸው ነበር። አሪየል ሳባር የተባሉት ጋዜጠኛ ስሚዝሶኒያን በተባለው መጽሔት ላይ አንዳንዶች እንዲህ ያለ አመለካከት ያላቸው ለምን እንደሆነ ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፦ “ተሰቅለው የሚገደሉት እንደ አረመኔ የሚቆጠሩ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ነበሩ። በመሆኑም አንዳንድ ምሁራን፣ ሮማውያን እንዲህ ያሉ ሰዎች በሥርዓት እንዲቀበሩ ይፈቅዳሉ ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር እንደሆነ ይሰማቸው ነበር።” ሮማውያን ሞት የተፈረደባቸው ወንጀለኞች እጅግ በሚያዋርድ መንገድ እንዲያዙ ይፈልጉ ነበር። በመሆኑም አስከሬናቸውን የዱር እንስሳት እንዲበሉት እዚያው እንጨት ላይ ይተዉታል። ከዚያም የተረፈው የአስከሬናቸው ክፍል በጋራ መቃብር ውስጥ ይጣላል።

ሆኖም የአርኪኦሎጂ ግኝቶች፣ ቢያንስ የአንዳንድ የተገደሉ አይሁዳውያን አስከሬን በተለየ መንገድ እንደተያዘ አሳይተዋል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን የተገደለ የአንድ ሰው አፅም በ1968 ተገኘ። አፅሙ የተገኘው በኢየሩሳሌም አቅራቢያ በሚገኝ አንድ የአይሁዳውያን የቤተሰብ መቃብር ውስጥ ነው። አፅሙ የተገኘው አፅም በሚቀመጥበት ሣጥን ውስጥ ነው። ከተገኘው አፅም መካከል የተረከዝ አጥንት ይገኝበታል። አጥንቱ 11.5 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ባለው የብረት ሚስማር ተቸንክሮ በእንጨት ሳንቃ ላይ ተጣብቆ ነበር። ኤሪየል ሳባር እንዲህ ብለዋል፦ “የሆካናን የተባለው ሰው የተረከዝ አጥንት፣ ኢየሱስ በመቃብር ውስጥ እንደተቀበረ ከሚገልጸው የወንጌል ዘገባ ትክክለኛነት ጋር በተያያዘ የነበረው ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ክርክር እልባት እንዲያገኝ አድርጓል። . . . የየሆካናን የተረከዝ አጥንት በኢየሱስ ዘመን ሮማውያን በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሰው በአይሁዳውያን ሥርዓት እንዲቀበር እንደፈቀዱ የሚያሳይ አንድ ማስረጃ ነው።”

ይህ የተረከዝ አጥንት ኢየሱስ በእንጨቱ ላይ ስለተሰቀለበት መንገድ ምን ይጠቁማል? ይህን ጉዳይ በተመለከተ ሰዎች የተለያየ አመለካከት አላቸው። ሆኖም ሞት ተፈርዶባቸው የተገደሉ አንዳንድ ወንጀለኞች እንዲሁ በጋራ መቃብር ውስጥ ከመወርወር ይልቅ በሥርዓት ይቀበሩ እንደነበር በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን። በእርግጥም የኢየሱስን አስከሬን ለቀብር እንዳዘጋጁትና በመቃብር ውስጥ እንዳኖሩት የሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ እምነት የሚጣልበት ነው። ማስረጃው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ትክክል እንደሆነ ያሳያል።

ከሁሉ በላይ ደግሞ ይሖዋ፣ ኢየሱስ በሀብታሞች መቃብር ውስጥ እንደሚቀበር ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ ደግሞም የአምላክ ቃል እንዳይፈጸም ሊያግድ የሚችል ማንም የለም።—ኢሳ. 53:9፤ 55:11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ