የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w22 ሐምሌ ገጽ 31
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሰላምን ሳይሆን ሰይፍን የሚያመጣው እውነት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • በሃይማኖት በተከፋፈለ ቤት ውስጥ ደስታን ጠብቆ መኖር ይቻላል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • በቤተሰባችሁ ውስጥ አምላክን ታስቀድማላችሁን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • የአንድን አስፋፊ የማያምን የትዳር ጓደኛ መርዳት ትችላላችሁ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
w22 ሐምሌ ገጽ 31

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ኢየሱስ “ሰላም ለማስፈን የመጣሁ አይምሰላችሁ” ሲል ምን ማለቱ ነበር?

ኢየሱስ የሰበከው የሰላም መልእክት ነው። ሆኖም በአንድ ወቅት ለሐዋርያቱ እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ “በምድር ላይ ሰላም ለማስፈን የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ የመጣሁት ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አይደለም። እኔ የመጣሁት ወንድ ልጅን ከአባቱ፣ ሴት ልጅን ከእናቷ እንዲሁም ምራትን ከአማቷ ለመለያየት ነው።” (ማቴ. 10:34, 35) ኢየሱስ እንዲህ ሲል ምን ማለቱ ነበር?

ኢየሱስ የቤተሰብ አባላትን የመለያየት ፍላጎት አልነበረውም። ሆኖም የእሱ ትምህርቶች በአንዳንድ ቤተሰቦች ውስጥ ክፍፍል ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ያውቅ ነበር። በመሆኑም የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆንና መጠመቅ የሚፈልጉ ሰዎች ውሳኔያቸው የሚያስከትለውን ውጤት መገንዘብ አለባቸው። ከማያምን የትዳር አጋራቸው ወይም ከሌሎች የቤተሰባቸው አባላት ተቃውሞ ካጋጠማቸው የኢየሱስን ትምህርቶች በታማኝነት መከተል ከባድ ሊሆንባቸው ይችላል።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ክርስቲያኖች “ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም” እንዲኖሩ ያበረታታል። (ሮም 12:18) ሆኖም የኢየሱስ ትምህርቶች በአንዳንድ ቤተሰቦች ውስጥ እንደ “ሰይፍ” ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ የሚሆነው አንዱ የቤተሰብ አባል የኢየሱስን ትምህርቶች ተቀብሎ ሌሎቹ ግን ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆኑ ወይም ከተቃወሙ ነው። እንዲህ ባለው ሁኔታ ውስጥ፣ እውነትን ለሚማረው ሰው ቤተሰቦቹ ‘ጠላቶች’ ይሆኑበታል።—ማቴ. 10:36

አንዲት ወጣት በድፍረት እናቷን ትታ ስትሄድ፤ እናቷ እየለመነቻት ነው። ወጣቷ “ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለውን መጽሐፍ ይዛለች።

በሃይማኖት በተከፋፈለ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት አንዳንድ ጊዜ ለይሖዋና ለኢየሱስ ያላቸውን ፍቅር የሚፈትን ሁኔታ ያጋጥማቸዋል። ለምሳሌ የማያምኑ ቤተሰቦቻቸው አንድን ሃይማኖታዊ በዓል እንዲያከብሩ ይገፋፏቸው ይሆናል። እንዲህ ያለ ፈተና ሲያጋጥማቸው ማንን እንደሚያስደስቱ መምረጥ ይኖርባቸዋል። ኢየሱስ “ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ሁሉ ለእኔ ሊሆን አይገባም” ብሏል። (ማቴ. 10:37) እርግጥ ነው፣ ኢየሱስ የእሱ ደቀ መዛሙርት መሆን የሚፈልጉ ሰዎች ለወላጆቻቸው ያላቸው ፍቅር ሊቀንስ እንደሚገባ መናገሩ አይደለም። ከዚህ ይልቅ በሕይወታቸው ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጡትን ነገር መምረጥ እንዳለባቸው ማሳሰቡ ነው። አማኝ ያልሆኑ ቤተሰቦቻችን ለይሖዋ የምናቀርበውን አምልኮ ቢቃወሙም እነሱን መውደዳችንን እንቀጥላለን። ሆኖም ቅድሚያ የሚሰጠው ለአምላክ ያለን ፍቅር እንደሆነ እንገነዘባለን።

የቤተሰብ ተቃውሞ በጣም ከባድ እንደሆነ አይካድም። ያም ቢሆን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት፣ ኢየሱስ “የመከራውን እንጨት የማይቀበልና የማይከተለኝ ሁሉ ለእኔ ሊሆን አይገባውም” በማለት የተናገራቸውን ቃላት አይዘነጉም። (ማቴ. 10:38) በሌላ አባባል ክርስቲያኖች የቤተሰብ ተቃውሞን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በፈቃደኝነት ከሚቀበሏቸው መከራዎች አንዱ አድርገው ይመለከቱታል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ መልካም ምግባራቸው አማኝ ያልሆኑ ቤተሰቦቻቸው አመለካከታቸውን እንዲቀይሩና ለመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ጆሯቸውን እንዲከፍቱ እንደሚያነሳሳቸው ተስፋ ያደርጋሉ።—1 ጴጥ. 3:1, 2

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ