መጠበቂያ ግንብ ላይ የሚወጡ ተጨማሪ ርዕሶች
በርካታ አስፋፊዎች ለስብሰባዎች ለመዘጋጀት JW Library® ይጠቀማሉ፤ እነዚህ አስፋፊዎች እያንዳንዱን የመጠበቂያ ግንብ የጥናት ርዕስ ለየብቻ ማግኘት በመቻላቸው ደስተኛ ናቸው። ሆኖም ብዙዎቹ የመጠበቂያ ግንብ የጥናት እትሞች መንፈሳዊ ምግብ የያዙ ተጨማሪ ርዕሶችም አሏቸው። JW Library ተጠቅመህ እነዚህን ርዕሶች ማግኘትና ማንበብ የምትችለው እንዴት ነው?
በእያንዳንዱ የመጠበቂያ ግንብ የጥናት ርዕስ መጨረሻ ላይ “ሌሎች ርዕሶች” የሚል ክፍል አለ። በዚህ ሥር የሚገኘውን “በዚህ እትም ውስጥ ያሉ ሌሎች ርዕሶች” የሚል ሊንክ ተጫን። የርዕስ ማውጫውን ስትመለከት የጥናት ርዕሶቹንና ቁጥራቸውን ማግኘት ትችላለህ። ከእነዚህ ውጭ ካሉት ተጨማሪ ርዕሶች መካከል የምትፈልገውን መርጠህ ክፈት።
በJW Library መነሻ ገጽ ላይ “አዲስ ነገር” በሚለው ክፍል ሥር አዲስ መጠበቂያ ግንብ በወጣ ቁጥር አውርድ። ያወረድከውን መጽሔት ከፍተህ የርዕስ ማውጫውን በመመልከት ከሁሉም ርዕሶች ጥቅም ማግኘት ትችላለህ።