የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp24 ቁጥር 1 ገጽ 3
  • ትክክል ወይስ ስህተት? በሁላችንም ፊት የተደቀነ ጥያቄ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትክክል ወይስ ስህተት? በሁላችንም ፊት የተደቀነ ጥያቄ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2024
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እምነት በማዳበር ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ አድርጉ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • አምላክን የሚያስከብር ውሳኔ አድርጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ጥሩ ውሳኔ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • መግቢያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2024
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2024
wp24 ቁጥር 1 ገጽ 3
ባለፈው ሥዕል ላይ የታየው ወጣት ከአንዲት የፓርክ ጠባቂ እርዳታ ሲያገኝ። መዳረሻው ወደሆነው ወደ ተራራው ጫፍ ለመድረስ የትኛውን መንገድ መከተል እንዳለበት ካርታ ተጠቅማ ታሳየዋለች።

ትክክል ወይስ ስህተት? በሁላችንም ፊት የተደቀነ ጥያቄ

ሄደህ ወደማታውቅበት ቦታ መጓዝ ብትፈልግ ምን ታደርጋለህ?

  1. 1. እንዲሁ በመሰለህ መንገድ ትሄዳለህ?

  2. 2. ሌሎች መንገዱን እንደሚያውቁት ተስፋ በማድረግ እነሱን ትከተላለህ?

  3. 3. እንደ ጂፒኤስ፣ እንደ ካርታ ወይም መንገዱን በትክክል እንደሚያውቅ ሰው ያለ አስተማማኝ መመሪያ ትጠቀማለህ?

የመጀመሪያዎቹን ሁለት አማራጮች ከተጠቀምን አንድ ቦታ ላይ መድረሳችን አይቀርም፤ ያም ቢሆን መድረስ የምንፈልግበት ቦታ ላይ ላንደርስ እንችላለን። ሦስተኛውን አማራጭ ከተጠቀምን ግን የምንፈልግበት ቦታ ላይ እንደምንደርስ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

ሕይወታችን ከጉዞ ጋር ሊመሳሰል ይችላል፤ ይህ ጉዞ ወደ አስደሳች መዳረሻ እንደሚመራን ተስፋ እናደርጋለን። ግባችን ላይ መድረስ አለመድረሳችን በዋነኝነት የተመካው ውሳኔዎችን ስናደርግ በምንከተለው መመሪያ ላይ ነው።

በሕይወታችን ውስጥ የምናደርጋቸው አብዛኞቹ ውሳኔዎች ያን ያህል ለውጥ የሚያመጡ አይደሉም፤ አንዳንዶቹ ውሳኔዎች ግን ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። እነዚህ ውሳኔዎች የምንከተላቸውን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ማለትም ትክክልና ስህተት ስለሆነው ነገር ያለንን አመለካከት ያንጸባርቃሉ። እንዲህ ያሉት ውሳኔዎች በእኛም ሆነ በምንወዳቸው ሰዎች ላይ ዘላቂ ውጤት ያመጣሉ፤ በጥሩ ወይም በመጥፎ። እነዚህ ውሳኔዎች እንደሚከተሉት ካሉ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ናቸው፦

  • የፆታ ግንኙነት እና ትዳር

  • ሐቀኝነት፣ ሥራ እና ገንዘብ

  • የልጆች አስተዳደግ

  • ከሌሎች ጋር ያለን ግንኙነት

በእነዚህ ጉዳዮች ረገድ የምታደርጋቸው ምርጫዎች ለአንተም ሆነ ለቤተሰብህ ዘላቂ ጥቅም እንደሚያስገኙ እርግጠኛ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?

በእያንዳንዳችን ፊት የሚከተለው ጥያቄ ተደቅኗል፦ ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር በተመለከተ ውሳኔ የማደርገው ምንን መሠረት አድርጌ ነው?

ይህ መጽሔት፣ መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ መመሪያ ይዟል የምንለው ለምን እንደሆነ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ አንተን ሊረዳህ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ