የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp24 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
  • ትክክል ወይስ ስህተት? ለእያንዳንዳችን የተተወ ምርጫ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትክክል ወይስ ስህተት? ለእያንዳንዳችን የተተወ ምርጫ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2024
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትክክል ወይም ስህተት ስለሆነው ነገር መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው መመሪያ በዘመናችንም ይሠራል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • የይሖዋ ሕዝቦች ጽድቅን ይወዳሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • መተማመን የምትችለው ማን ባወጣቸው መሥፈርቶች ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ትክክል ወይስ ስህተት? መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ መመሪያ ይሰጠናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2024
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2024
wp24 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
ባለፉት ርዕሶች ላይ የታየው ወጣት የተራራው ጫፍ ላይ ከደረሰ በኋላ በደስታ ወደ ርቀት ሲመለከት።

ትክክል ወይስ ስህተት? ለእያንዳንዳችን የተተወ ምርጫ

የምንከተለው የሥነ ምግባር መሥፈርት በወደፊት ሕይወታችን ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። ይሖዋ አምላክ ይህን ያውቃል። በእሱ መሥፈርቶች እንድንመራ የሚፈልገው ለዚህ ነው።

ይሖዋ ሰላማዊና አስደሳች ሕይወት እንድንመራ ይፈልጋል።

“የሚጠቅምህን ነገር የማስተምርህ፣ ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህ እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ። ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው! እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል።”—ኢሳይያስ 48:17, 18

አምላክ ፈጣሪያችን እንደመሆኑ መጠን ሕይወታችንን መምራት የምንችልበትን ከሁሉ የተሻለ መንገድ ያውቃል። መመሪያውን እንድንከተል የሚጠይቀን እንደሚጠቅመን ስለሚያውቅ ነው። የአምላክን ትእዛዛት የምንከተል ከሆነ ‘ውሳኔዬ ጥሩ ውጤት ያስገኝ ይሆን?’ ብለን አንሰጋም። ምንጊዜም ሰላምና ደስታ የሚያስገኘውን ትክክለኛ ምርጫ እናደርጋለን።

ይሖዋ ከአቅማችን በላይ አይጠብቅብንም።

“እኔ ዛሬ የማዝህ ይህ ትእዛዝ ለአንተ ያን ያህል ከባድ አይደለም፤ ከአንተም የራቀ አይደለም።”—ዘዳግም 30:11

በአምላክ የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ለመመራት በአስተሳሰባችንና በድርጊታችን ላይ ለውጥ ማድረግ ሊኖርብን ይችላል። ይሁንና ይሖዋ የሚጠብቅብን ነገር ከአቅማችን በላይ አይደለም። ደግሞም እሱ ፈጣሪያችን እንደመሆኑ መጠን አቅማችንን ያውቃል። ይሖዋን ይበልጥ እያወቅነው ስንሄድ ‘ትእዛዛቱ ከባድ እንዳልሆኑ’ እንገነዘባለን።—1 ዮሐንስ 5:3

ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች “ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅመው አንዲትን ሴት መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስጠኑ።

ይሖዋ በእሱ መሥፈርቶች ለመመራት የሚመርጡ ሰዎችን እንደሚረዳ ቃል ገብቷል።

“‘አትፍራ። እረዳሃለሁ’ የምልህ እኔ፣ አምላክህ ይሖዋ ቀኝ እጅህን ይዣለሁና።”—ኢሳይያስ 41:13

አምላክ ስለሚረዳን የእሱን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች አክብረን መኖር እንችላለን። በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ማበረታቻና ተስፋ በመስጠት ይረዳናል።

በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች መመራታቸው ሕይወታቸውን እንዳሻሻለው አስተውለዋል። አንተስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላለው ጠቃሚ ምክር ይበልጥ ለመማር ለምን አትሞክርም? ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ብሮሹር በማጥናት መጀመር ትችላለህ። ብሮሹሩ jw.org ላይ በነፃ ይገኛል። ብሮሹሩ የሚከተሉትን ምዕራፎች ይዟል፦

  • መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

  • መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ብርሃን ይፈነጥቃል

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እምነት መጣል ትችላለህ?

የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ስትመረምር ዘመን ያለፈበት መጽሐፍ እንዳልሆነ ትገነዘባለህ፤ ከዚህ ይልቅ “አሁንም ሆነ ለዘላለም፣ ምንጊዜም አስተማማኝ” ነው። (መዝሙር 111:8) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መከተል ከሁሉ የተሻለ የሕይወት ጎዳና ነው። ያም ቢሆን አምላክ እንዲህ እንድናደርግ አያስገድደንም። (ዘዳግም 30:19, 20፤ ኢያሱ 24:15) ይህ ለእያንዳንዳችን የተተወ ምርጫ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ