የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w24 ግንቦት ገጽ 32
  • የፍትሕ መጓደልን በጽናት መቋቋም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የፍትሕ መጓደልን በጽናት መቋቋም
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “የምድር ሁሉ ዳኛ” ምንጊዜም ትክክል የሆነውን ነገር ያደርጋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • ‘እንዴት ይህን ክፉ ድርጊት እፈጽማለሁ?’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ይሖዋ ስኬታማ እንድትሆኑ ይረዳችኋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • አምላክን የታዘዘ ባሪያ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
w24 ግንቦት ገጽ 32

የጥናት ፕሮጀክት

የፍትሕ መጓደልን በጽናት መቋቋም

ዘፍጥረት 37:23-28፤ 39:17-23⁠ን አንብብ፤ ከዚያም ዮሴፍ የደረሰበትን የፍትሕ መጓደል የተቋቋመው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

አውዱን መርምር። ዮሴፍ የፍትሕ መጓደል የደረሰበት ለምንድን ነው? (ዘፍ. 37:3-11፤ 39:1, 6-10) ዮሴፍ የደረሰበትን የፍትሕ መጓደል መቋቋም ያስፈለገው ለምን ያህል ጊዜ ነው? (ዘፍ. 37:2፤ 41:46) በዚያ ወቅት ይሖዋ ለዮሴፍ ምን አድርጎለታል? ምንስ አላደረገለትም?—ዘፍ. 39:2, 21፤ w23.01 17 አን. 13

በጥልቀት ምርምር አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ዮሴፍ የጶጢፋር ሚስት ለሰነዘረችበት የሐሰት ክስ ምንም ዓይነት የመከላከያ መልስ እንደሰጠ አይናገርም። የሚከተሉት ጥቅሶች፣ ዮሴፍ ዝም ለማለት የመረጠው ለምን እንደሆነ ወይም ሁሉም ዝርዝር ጉዳዮች ዘገባው ላይ እንዲካተቱ መጠበቅ የሌለብን ለምን እንደሆነ ለማስተዋል የሚረዱን እንዴት ነው? (ምሳሌ 20:2፤ ዮሐ. 21:25፤ ሥራ 21:37) ዮሴፍ የደረሰበትን የፍትሕ መጓደል በጽናት እንዲቋቋም የረዱት የትኞቹ ባሕርያት ሊሆኑ ይችላሉ?—ሚክ. 7:7፤ ሉቃስ 14:11፤ ያዕ. 1:2, 3

ትምህርቱን ለማስተዋል ሞክር። ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  • ‘የኢየሱስ ደቀ መዝሙር እንደመሆኔ መጠን ምን ዓይነት የፍትሕ መጓደል እንደሚደርስብኝ መጠበቅ ይኖርብኛል?’ (ሉቃስ 21:12, 16, 17፤ ዕብ. 10:33, 34)

  • ‘የሚደርስብኝን የፍትሕ መጓደል በተሳካ ሁኔታ ለመቋቋም መዘጋጀት የምችለው እንዴት ነው?’ (መዝ. 62:7, 8፤ 105:17-19፤ w19.07 2-7)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ