የጥናት ፕሮጀክት
በትጋት በማጥናት ነቅተህ ጠብቅ
ዳንኤል 9:1-19ን አንብብ፤ ከዚያም በትጋት ማጥናት ያለውን አስፈላጊነት ለማስተዋል ሞክር።
አውዱን መርምር። ከዚያ ጥቂት ቀደም ብሎ የትኞቹ ነገሮች ተከስተው ነበር? እነዚህ ነገሮችስ በዳንኤል ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድረውበታል? (ዳን. 5:29–6:5) በዳንኤል ቦታ ብትሆን ኖሮ ምን ይሰማህ ነበር?
በጥልቀት ምርምር አድርግ። ዳንኤል የትኞቹን ‘ቅዱሳን መጻሕፍት’ መርምሮ ሊሆን ይችላል? (ዳን. 9:2፤ w11 1/1 22 አን. 2) ዳንኤል የራሱን እና የእስራኤልን ብሔር ኃጢአት የተናዘዘው ለምንድን ነው? (ዘሌ. 26:39-42፤ 1 ነገ. 8:46-50፤ dp 182-184) ዳንኤል ያቀረበው ጸሎት የአምላክን ቃል በትጋት ያጠና እንደነበር የሚያሳየው እንዴት ነው?—ዳን. 9:11-13
ትምህርቱን ለማስተዋል ሞክር። ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦
‘በዓለም ላይ በሚከሰቱ ነገሮች ትኩረቴ እንዳይከፋፈል ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?’ (ሚክ. 7:7)
‘እንደ ዳንኤል የአምላክን ቃል በትጋት ማጥናቴ የሚጠቅመኝ እንዴት ነው?’ (w04 8/1 12-13 አን. 17)
‘ነቅቼ ለመጠበቅ የትኞቹን ርዕሰ ጉዳዮች በግል ጥናቴ ላይ ማካተት እችላለሁ?’ (ማቴ. 24:42, 44፤ w12 8/15 5 አን. 7-8)