የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w24 ጥቅምት ገጽ 30
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ንጉሥ ዳዊትና ሙዚቃ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ሙዚቃ—ልብን ደስ የሚያሰኝ የአምላክ ስጦታ
    ንቁ!—2008
  • አምላክን ደስ የሚያሰኝ ሙዚቃ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • የማዳምጠው ሙዚቃ ለውጥ ያመጣል?
    የወጣቶች ጥያቄ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
w24 ጥቅምት ገጽ 30
ሙዚቀኛ የሆኑ እስራኤላውያን መለከት በመንፋት፣ በገና በመደርደርና ጮክ ብለው በመዘመር ለይሖዋ አምልኮ ሲያቀርቡ።

ይህን ያውቁ ኖሯል?

የጥንት እስራኤላውያን ለሙዚቃ ምን ያህል ቦታ ይሰጡ ነበር?

በጥንት እስራኤላውያን ባሕል ውስጥ ሙዚቃ ጉልህ ቦታ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሙዚቃ መሣሪያ ስለሚጫወቱና መዝሙር ስለሚዘምሩ ሰዎች በብዙ ቦታዎች ላይ ይናገራል። አንድ አሥረኛ የሚሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የያዙት መዝሙሮች ናቸው፤ ከእነዚህ መካከል የመዝሙር መጽሐፍ፣ መኃልየ መኃልይ እና ሰቆቃወ ኤርምያስ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። ሚዩዚክ ኢን ቢብሊካል ላይፍ የተባለው መጽሐፍ እንደሚገልጸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ “እስራኤላውያን በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ሙዚቃን ይጠቀሙ እንደነበር በግልጽ ያሳያል።”

ሙዚቃ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ። እስራኤላውያን ስሜታቸውን ለመግለጽ ሙዚቃን ይጠቀሙ ነበር። (ኢሳ. 30:29) ሴቶች በነገሥታት የሹመት ሥነ ሥርዓት፣ በበዓላትና በድል ወቅት አታሞ እየመቱ በደስታ ይዘፍኑና ይጨፍሩ ነበር። (መሳ. 11:34፤ 1 ሳሙ. 18:6, 7፤ 1 ነገ. 1:39, 40) በተጨማሪም እስራኤላውያን በሐዘን ወቅት ስሜትን የሚገልጹ ሙሾዎችን ያወርዱ ነበር። (2 ዜና 35:25) በግልጽ ማየት እንደሚቻለው እስራኤላውያን ሙዚቃ በጣም ይወዱ ነበር።

ሙዚቃ በቤተ መንግሥት ውስጥ። የእስራኤል ነገሥታት ሙዚቃ መስማት ያስደስታቸው ነበር። ንጉሥ ሳኦል ሙዚቃ እንዲጫወትለት ዳዊትን ወደ ቤተ መንግሥቱ አስጠርቶታል። (1 ሳሙ. 16:18, 23) ዳዊት ራሱ ንጉሥ ከሆነ በኋላ ደግሞ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ፈልስፏል፤ ደስ የሚሉ መዝሙሮችን አቀናብሯል፤ እንዲሁም በይሖዋ ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚጫወቱ የሙዚቀኞች ቡድኖችን አደራጅቷል። (2 ዜና 7:6፤ አሞጽ 6:5) ንጉሥ ሰለሞንም በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ወንድና ሴት ዘፋኞች ነበሩት።—መክ. 2:8

ሙዚቃ በአምልኮ ውስጥ። በዋነኝነት ደግሞ እስራኤላውያን ሙዚቃን ለይሖዋ አምልኮ ይጠቀሙበት ነበር። እንዲያውም በኢየሩሳሌም ባለው ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚጫወቱ 4,000 ሙዚቀኞች ነበሩ። (1 ዜና 23:5) ሲምባል፣ ባለ አውታር መሣሪያዎችና በገና ይጫወቱ እንዲሁም መለከት ይነፉ ነበር። (2 ዜና 5:12) ሆኖም በሙዚቃ ተጠቅመው ይሖዋን ያመልኩ የነበሩት እነዚህ የሠለጠኑ ሙዚቀኞች ብቻ አይደሉም። በርካታ እስራኤላውያን ዓመታዊ በዓላትን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም በሚሄዱበት ወቅት “ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር” ተብለው የሚጠሩትን መዝሙሮች ይዘምሩ እንደነበር ከሁኔታዎች መረዳት ይቻላል። (መዝ. 120–134) በተጨማሪም አንዳንድ የአይሁድ መዛግብት እንደሚገልጹት እስራኤላውያን የፋሲካን ራት በሚበሉበት ወቅት የሃሌል መዝሙሮችንa ይዘምሩ ነበር።

በዛሬው ጊዜም ቢሆን የአምላክ ሕዝቦች ለሙዚቃ ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ። (ያዕ. 5:13) መዝሙር መዘመር የአምልኳችን ክፍል ነው። (ኤፌ. 5:19) ሙዚቃ ከእምነት አጋሮቻችን ጋር ያቀራርበናል። (ቆላ. 3:16) በተጨማሪም በመከራ ውስጥ ስንሆን ያጠናክረናል። (ሥራ 16:25) ሙዚቃ በይሖዋ ላይ ያለንን እምነትና ለእሱ ያለንን ፍቅር የምናሳይበት ግሩም መንገድ ነው።

a አይሁዳውያን ይሖዋን ለማወደስ የሚዘመሩትን ከመዝሙር 113 እስከ 118 ያሉትን መዝሙሮች “የሃሌል መዝሙሮች” ብለው ይጠሯቸዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ