ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች
ከሥዕላዊ መግለጫዎች የተሟላ ጥቅም ማግኘት
ጽሑፎቻችን አስፈላጊ ነጥቦችን በሚያስተምሩ ሥዕላዊ መግለጫዎች የተሞሉ ናቸው። ከእነዚህ ሥዕላዊ መግለጫዎች የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?
አንቀጾቹን ከማንበብህ በፊት ሥዕላዊ መግለጫዎቹን ተመልከት። ሥዕሎቹ የማወቅ ጉጉትህን ሊቀሰቅሱትና ጽሑፉን ለማንበብ ሊያነሳሱህ ይችላሉ። የአንድ ምግብ ማራኪ አቀራረብ ገና ስናየው ለመብላት እንደሚያጓጓን ሁሉ ለንባብም እንደዚያው ነው። ስለዚህ ‘ምን ይታየኛል?’ እያልክ ራስህን ጠይቅ።—አሞጽ 7:7, 8
አንቀጾቹን በምታነብበት ጊዜ ያ ሥዕላዊ መግለጫ የተመረጠው ለምን እንደሆነ አስብ። ከሥዕሉ በታች ያለውን ሐሳብና የሥዕሉን መግለጫ አንብብ። ሥዕላዊ መግለጫው ከሚብራራው ርዕሰ ጉዳይና ከግል ሕይወትህ ጋር የሚዛመደው እንዴት እንደሆነ አስብ።
አንብበህ ከጨረስክ በኋላ ቁልፍ ነጥቦቹን ለመከለስ ሥዕላዊ መግለጫዎቹን ተጠቀም። እያንዳንዱን ሥዕል መልሰህ ወደ አእምሮህ ለማምጣትና ሥዕሉ የሚያስተላልፈውን ትምህርት ለማስታወስ ሞክር።
በዚህ መጽሔት ውስጥ ያሉትን ሥዕሎች መለስ ብለህ በማየት የሚያስተላልፉትን ነጥብ ለማስታወስ ለምን አትሞክርም?