የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 34
  • አምላክ ለጸሎቴ መልስ ይሰጣል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ለጸሎቴ መልስ ይሰጣል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • በጸሎት እርዳታ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 34

አምላክ ለጸሎቴ መልስ ይሰጣል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አዎ፣ መልስ ይሰጣል። ከመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በአሁኑ ጊዜ ካሉ ሰዎች ተሞክሮ መረዳት እንደሚቻለው አምላክ ለጸሎታችን መልስ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “[አምላክ] ለሚፈሩት ፍላጎታቸውን ይፈጽማል፤ ጩኸታቸውን ይሰማል፤ ያድናቸዋልም።” (መዝሙር 145:19) ይሁንና አምላክ ጸሎትህን ሰምቶ መልስ መስጠቱ በአብዛኛው የተመካው በአንተ ላይ ነው።

አምላክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገር

  • ወደ ኢየሱስ፣ ወደ ማርያም፣ ወደ ቅዱሳን፣ ወደ መላእክት ወይም ለምስሎች ሳይሆን ወደ አምላክ መጸለይ ይኖርብናል። ‘ጸሎትን የሚሰማው’ ይሖዋ አምላክ ብቻ ነው።​—መዝሙር 65:2

  • ከአምላክ ፈቃድ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት መሥፈርቶች ጋር በሚስማማ መንገድ መጸለይ ይጠበቅብናል።​—1 ዮሐንስ 5:14

  • የኢየሱስን ሥልጣን በመቀበል በእሱ ስም መጸለይ ይኖርብናል። ኢየሱስ “በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” ብሏል።​—ዮሐንስ 14:6

  • በእምነት መጸለይ ይኖርብናል፤ አስፈላጊ ከሆነም እምነት እንዲጨመርልን መጸለይ እንችላለን።​—ማቴዎስ 21:22፤ ሉቃስ 17:5

  • በትህትና ከልባችን መጸለይ ይኖርብናል። መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር በከፍታ ስፍራ ቢሆንም፣ ዝቅ ያለውን ይመለከተዋል” ይላል።​—መዝሙር 138:6

  • ያለማቋረጥ መጸለይ ይኖርብናል። ኢየሱስ “ደጋግማችሁ ለምኑ፣ ይሰጣችኋል” ብሏል።​—ሉቃስ 11:9

አምላክ ቦታ የማይሰጠው ነገር

  • ዘርህ ወይም ዜግነትህ። ‘አምላክ አያዳላም፤ ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና የጽድቅ ሥራ የሚሠራ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።’​—የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35

  • አቋቋምህ ወይም አቀማመጥህ። ተቀምጠህ፣ በግንባርህ ተደፍተህ፣ ተንበርክከህ ወይም ቆመህ መጸለይ ትችላለህ።​—1 ዜና መዋዕል 17:16፤ ነህምያ 8:6፤ ዳንኤል 6:10፤ ማርቆስ 11:25

  • ድምፅህን አሰምተህ መጸለይህ ወይም በልብህ መጸለይህ። አምላክ ሌሎች ሰዎች ሳያስተውሉ በልባችን እንኳ የምናቀርባቸውን ጸሎቶች ይሰማል።​—ነህምያ 2:1-6

  • ያሰሰበህ ጉዳይ ከባድ ወይም ቀላል መሆኑ። አምላክ ‘ስለ እኛ ስለሚያስብ የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ በእሱ ላይ እንድንጥል’ አበረታቶናል።​—1 ጴጥሮስ 5:7

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ