የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 39
  • ክርስቲያኖች የሕክምና እርዳታ ይቀበላሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ክርስቲያኖች የሕክምና እርዳታ ይቀበላሉ?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • የምትመርጠው የሕክምና ዓይነት ለውጥ ያመጣልን?
    ንቁ!—2001
  • የይሖዋ ምሥክሮች የሚሰጣቸውን የሕክምና እርዳታ ይቀበላሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የይሖዋ ምሥክሮች ስለ ሕክምና ያላቸው አቋም ምንድን ነው?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • ከመናፍስታዊ ድርጊቶች መራቅ ያለብህ ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 39

ክርስቲያኖች የሕክምና እርዳታ ይቀበላሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

እንዴታ! ኢየሱስ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም” በማለት የተናገረው ሐሳብ ተከታዮቹ የሕክምና እርዳታ መቀበል እንደሚችሉ ይጠቁማል። (ማቴዎስ 9:12) መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና መጽሐፍ ባይሆንም አምላክን ለማስደሰት የሚፈልጉ ሰዎች ሊከተሏቸው የሚገቡ መመሪያዎችን ይዟል።

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ

1. ይህ ሕክምና ምን ነገሮችን እንደሚያካትት አውቃለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ ‘ሁሉን ከማመን’ ይልቅ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ጥረት እንድናደርግ ይመክረናል።​—ምሳሌ 14:15

2. ሌሎች ሐኪሞችን ማማከር ያስፈልገኝ ይሆን? በተለይ ሕመሙ ከባድ ከሆነ “ብዙ አማካሪዎች” መኖራቸው ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።​—ምሳሌ 15:22

3. ሕክምናው ‘ከደም ራቁ’ የሚለውን የመጽሐፍ የቅዱስ ምክር እንድጥስ ያደርገኛል?​—የሐዋርያት ሥራ 15:20

4. ምርመራው ወይም ሕክምናው ከመናፍስታዊ ድርጊቶች ጋር ንክኪ አለው? መጽሐፍ ቅዱስ ‘መናፍስታዊ ድርጊትን’ ያወግዛል። (ገላትያ 5:19-21) ሕክምናው ከመናፍስታዊ ድርጊቶች ጋር ንክኪ ይኖረው እንደሆነ ለማወቅ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  • ሕክምናውን የሚሰጠው ሰው መናፍስታዊ ድርጊቶችን ይፈጽማል?

  • ሕክምናውን የሚሰጠው ሰው፣ ግለሰቡ በበሽታ የተያዘው አማልክት ስለተቆጡ ወይም ጠላቶቹ መተት ስላደረጉበት እንደሆነ ይናገራል?

  • መድኃኒቱ ሲዘጋጅ ወይም ሲወሰድ መሥዋዕት፣ ድግምት አሊያም ሌላ ዓይነት መናፍስታዊ ድርጊት ወይም ዕቃ ጥቅም ላይ ይውላል?

5. የጤናዬ ጉዳይ ከልክ በላይ ያሳስበኛል? መጽሐፍ ቅዱስ “ምክንያታዊነታችሁ በሰው ሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሁን” የሚል ምክር ይሰጣል። (ፊልጵስዩስ 4:5) ምክንያታዊ መሆን እንደ መንፈሳዊ ነገሮች ባሉ “ይበልጥ አስፈላጊ [በሆኑ] ነገሮች” ላይ እንድታተኩር ይረዳሃል።​—ፊልጵስዩስ 1:10፤ ማቴዎስ 5:3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ