የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 47
  • አጋንንት በእርግጥ አሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አጋንንት በእርግጥ አሉ?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መላእክትንና አጋንንትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ኢየሱስ ከአጋንንት የበለጠ ኃይል አለው
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • መንፈሳዊ ፍጡራን—ሊጠቅሙን ወይም ሊጎዱን የሚችሉት እንዴት ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • መንፈሳዊ ፍጥረታት ሊጠቅሙን ወይም ሊጎዱን የሚችሉት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 47

አጋንንት በእርግጥ አሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አጋንንት በእርግጥ አሉ። አጋንንት በአምላክ ላይ ያመፁ መንፈሳዊ ፍጥረታት ሲሆኑ ‘ኃጢአት የሠሩ መላእክት’ ተብለው ተጠርተዋል። (2 ጴጥሮስ 2:4) ራሱን ጋኔን ያደረገው የመጀመሪያው መልአክ ሰይጣን ዲያብሎስ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን መልአክ ‘የአጋንንት አለቃ’ በማለት ይጠራዋል።—ማቴዎስ 12:24, 26

በኖኅ ዘመን የነበረው ዓመፅ

መጽሐፍ ቅዱስ በኖኅ ዘመን ከደረሰው የጥፋት ውኃ በፊት መላእክት እንዳመፁ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ “የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ውብ ሆነው አዩአቸው፤ ከመካከላቸውም የመረጧቸውን አገቡ።” (ዘፍጥረት 6:2) እነዚህ ክፉ ወይም ዓመፀኛ መላእክት ከሴቶች ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ሲሉ በሰማይ የነበረውን “ትክክለኛ መኖሪያቸውን” ትተው የሰው አካል ለበሱ።​—ይሁዳ 6

የጥፋት ውኃው ሲመጣ ዓመፀኞቹ መላእክት የለበሱትን ሰብዓዊ አካል በመተው ወደ ሰማይ ተመለሱ። ይሁንና አምላክ ከቤተሰቡ አባረራቸው። በተጨማሪም ድጋሚ ሰብዓዊ አካል እንዳይለብሱ በመከልከል ቀጣቸው።​—ኤፌሶን 6:11, 12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ